ባህር ሀይል⁉️
ትላንት አርብ በኢትዮጵያ የታዩ ሁለት ቪድዮዎች የአለምን ትኩረት ስበዋል።
አንድ ለጦርነት የተዘጋጀ የኢትዮጵያ የጦር መርከብ ትክክለኛ ቦታው ባልተገለጸ ቦታ ላይ በጦር መሳሪያ ታጭቆ ሲጓዝ የሚያሳይ ቪድዮ ተለቆ መነጋገሪያ ሆኗል።
ከዚህ ቪድዮ በኋላ አርብ አመሻሹን ደግሞ ሌላ አነስተኛ የውጊያ ጀልባ የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል የሚል የተጻፈበት ቪድዮ ታይቷል። ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው ግን ቀደም ብሎ የወጣው ቪድዮ ላይ የታየው የጦር መርከብ ነው።
የጦር መርከቡ የት ቦታ እንዳለም ሆነ ወዴት እያቀና እንዳለ ያልገለጸው ቪድዮ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ የባሕር ሃይል አባል መርከቡ ላይ ሆኖ መርከቡ የኢትዮጵያ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን እና ለውጊያ የተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጹ ምስሎች ሲቀርጽ ታይቷል።
ከቪድዮ ለመረዳት እንደተቻለው ከሆነ መርከቡ ግዙፍ ሲሆን በትንሹ በ ሶስት አቅጣጫ ለመተልኮስ የተዘጋጁ ተተኳሽ ሚሳኤሎችን ታጥቋል። የጦር መርከቡ እየሄደ ያለው ወዴት ነው የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና ማዘዣ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ሪፖርተር ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
@Addis_Reporter