ደብዛው ጠፍቶ የቆየው አነስተኛ አውሮፕላን ስብርባሪው ተገኘ።
ከቀናት በፊት በአሜሪካ አላስካ ግዛት 9 መንገደኞችን እና 1 አብራሪን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ደብዛው ጠፍቶ ከቆየ በኃላ በአየር እና ምድር በተደረገ አሰሳ ስብርባሪው ተገኝቷል።
በአደጋው በሕይወት የተረፈ ሰው የለም።
የ3 ሰዎች አስክሬን በነፍስ አድን ሰራተኞች ተገኝቷል።
ይህ አደጋ በአሜሪካ ከ1 ሳምንት ባነሰ ጊዜ የደረሰ 3ኛው የአቬዬይሽን አደጋ መሆኑን የቪኦኤ ዘገባ ያሳያል።
በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከስክሶ በህይወት የተገኘ እንደሌለ ይታወቃል።
ከዚህ አደጋ በፊት ደግሞ በዋሽንግቶን ዲሲ 60 መንገደኞች እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን 3 ሰዎች ከያዘ የጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ አንድም ሰው በህይወት አለመገኘቱ መገለጹ ይታወሳል።
@Addis_Reporter