ይነበብ‼️
አንዱ የ400 ብር የመብራት አገልግሎት ቻርጅ ለማድረግ መብራት ኋይል ሄዶ የገጠመው የሰርቪስና የታክስ ብዛት ይህንን ይመስላል።
ሰርቪስ ቻርጅ 15.65
የተቆጣጣሪ ክፍያ 1.95
የኢቢሲ ቴሌቭዠን 10
ቫት ዶሜስቲክ 336.32
ቫት ሰርቪስ ቻርጅ 2.35
በድምሩ ከ 400 ብር ላይ በርካታ ታክሶችና ቅንስናሾች 366. 27 ከፍሎ ለመብራት አገልግሎት ብር 33 ከ73 ቻርጅ ተደርጎለት ተመልሷል። (መረጃው ተያይዟል)
የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ይሏችኋል ይሄ ነው። በቻርጅ ላይ ቻርጅ፣ በቫት ላይ ቫት፣ በታክስ ላይ ታክስ፣ በክፍያ ላይ ክፍያ! እንዲህ ያለ ነገር የየትኛው ሀገር ተመክሮ ይሆን ?
እንደኔ እንደኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በየወሩ መጨረሻ በመገናኛ ብዙሃን ጥሪ እየተደረገልን ቤታችን ሳንገባ አንድም ሳንቲም ሳናጎድል ደመወዛችንና ገቢያችንን ለወረዳ ፋይናንስ ብናስረክብ የሚሻል ይመስለኛል ?!
ማለቴ፣ እኛንም እናንተንም ከማሰብ፣ ከመጨነቅ ከውጣ ውረድና ከድካም ይገላግለናል። ደረሰኝ ምናምንስ ለምን ያስፈልጋል። "ኪሳችን ኪሳችሁ። ቤታችን ቤታችሁ እንዲያው አንድ አምሳልና አንድ አካል ሆነን የለ ¡¡¡"
ያለ ገቢ መኖር እንዴት እንደሚቻል በጾም በጸሎት እስኪገለጽልን ደረስ ደግሞ ደመወዛችንን ብቻ ሳይሆን በነካ እጃችሁ ቤተሰቦቻችንንም ጭምር መረከቡን እንዳትረሱት። ሲመቸንና ስራ በሌለን ጊዜ፣ በበዓልና በእረፍት ቀን እየመጣን እንጠይቃቸዋለን
የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ሙሼ ሰሙ
@Addis_Reporter