ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ 15 ሚሊየን ዶላር ለገሰች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ሰላምና መረጋጋት በሁሉም መስክ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡
በሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው የሱዳንን ቀውስ ለማስቆም በተለይም በረመዳን የጾም ወቅት የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለሱዳናውያን እንዲደርስ ለማስቻል የተደረገ ነው።
በጉባኤው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ሱዳን ጎረቤት ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ጠንካራ ቁርኝት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሱዳን ህዝብ ጎን ትቆማለች፤ ባላት አቅምም የምታደረገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ 15 ሚሊየን ዶላር ለግሳለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በበኩሏ ተጨማሪ 200 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሰጥታለች።
በጉባኤው የኬንያው ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አልናህያን፣ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተካፍለዋል።
@Addis_Reporter