የኮንዶም እጥረት መፍትሄ አገኘ፡ ለአንድ
ዓመት ተኩል የሚሆን በቂ አቅርቦት ገባ
በኢትዮጵያ አጋጥሞ የነበረውን የኮንዶም እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ግብአቶች እጥረት ለመቅረፍ ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለ18 ወራት የሚሆን ሰፊ በቂ አቅርቦት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የእርዳታ አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምክንያት ተፈጥሮ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት፣ ተቋሙ በግዥና ሎጅስቲክስ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም የአለም ጤና ድርጅት መስፈርቶችን ያሟላ ዘመናዊ ማዕከላዊ መጋዘን በመገንባት የአቅርቦቱ ጥራት ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቅ ተደርጓል።
ይህ የተገዛው አቅርቦት በሶሻል ማርኬቲንግ አሰራር ድጎማ እየተደረገለት ለፋርማሲዎች፣ ለግል ጤና ተቋማት፣ ለሆቴሎች እና ለኪዮስኮች በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሰራጨ ይገኛል። ከዚህም በላይ በ7 የክልል ማዕከላት ጥያቄ በቀረበ በ24 ሰዓት ውስጥ የማድረስ ፈጣን ስርዓትና የደንበኞች የአጭር ስልክ ጥሪ ማዕከል በመዘርጋቱ ሕብረተሰቡ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችል ተመላክቷል።
@Addis_Reporter