በረሮን እና አይጥን ያለ ከባድ ኬሚካል ለመቆጣጠር የሚረዱ የቤት ውስጥ እና የመከላከያ ዘዴዎች ይፋ ተደረጉ
በረሮዎች እና አይጦች በጤና እና በምግብ ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመከላከል፣ ቤተሰብን፣ ህፃናትን እና ምግብን ለከባድ ኬሚካሎች ሳያጋልጡ በቤት ውስጥ በሚገኙ ቀላል ነገሮች እነዚህን ተባዮች መቆጣጠር የሚቻልባቸው መንገዶች ተጠቆሙ።
በረሮዎችን ለማጥፋት እና ለማባረር እኩል መጠን ያለው ቤኪንግ ሶዳ እና የተፈጨ ስኳር (1 ለ 1) በደረቁ ቀላቅሎ ከሲንክ ስር እና ከፍሪጅ ጀርባ በትናንሽ ክዳኖች ማስቀመጥ እንደሚቻል ተገልጿል። ስኳሩ በረሮዎችን ሲስብ ቤኪንግ ሶዳው ሆድ ውስጥ ካለው አሲድ ጋር በመዋሃድ ጋዝ በመፍጠር ያጠፋቸዋል፤ ሆኖም እርጥበት እንዳይነካው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ነው የተባለው።
በተጨማሪም 1 የሾርባ ማንኪያ ቦሪክ አሲድ፣ 1 የሾርባ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት እና 1 የሾርባ ማንኪያ ስኳር በትንሽ ውሃ አቡክቶ ትናንሽ ኳሶች በመሥራት ህፃናትና የቤት እንስሳት በማይደርሱባቸው ስንጥቆች እና ከዕቃዎች ስር ማስቀመጥ እንደሚቻል ተመልክቷል። ቦሪክ አሲድ የምግብ መፈጨት ሥርዓትን የሚያውክ ቢሆንም፣ አነስተኛ መርዛማነት ስላለው በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል 3 እስከ 4 የሾርባ ማንኪያ ፈሳሽ የዕቃ ማጠቢያ ሳሙና ከውሃ ጋር በጥብጠው በሚታዩ በረሮዎች ላይ ሲረጩ የመተንፈሻ ቀዳዳዎቻቸውን በመዝጋት በሰከንዶች ውስጥ እንደሚያፍናቸው ተገልጿል። ቅርንፉድ እና የሾርባ ቅጠል ደግሞ በጠንካራ ሽታቸው በረሮዎችን ስለሚያባርሩ በእህል ማስቀመጫዎች እና በኩሽና መደርደሪያዎች አካባቢ ማስቀመጥ ውጤታማ መሆኑ ተጠቅሷል።
አይጦችን ለማባረር የባህር ዛፍ ወይም የፔፐርሚንት ዘይት የተነከረ ጥጥ በሚገቡባቸው ቀዳዳዎች እና በሮች ስር ማስቀመጥ እንደሚቻል ተገልጿል፤ ሽታው የማሽተት ችሎታቸውን ስለሚያውክ አካባቢውን ይለቃሉ፤ ሆኖም በየ5 እስከ 7 ቀኑ ማደስ እና ለድመቶችና ለውሾች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በርበሬ ወይም ቁንዶ በርበሬ አይጦች በሚመላለሱባቸው የግድግዳ ጥጎች እና መግቢያ ክፍተቶች ላይ መነስነስ ጠቃሚ ቢሆንም፣ ህፃናት በሚድሁበት ወለል ላይ እንዳይጠቀሙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ከአይጥ መርዝ ይልቅ ወጥመድ መጠቀም እንደሚመረጥ የተገለጸ ሲሆን፣ ምክንያቱም መርዝ የበላ አይጥ ግድግዳ ወይም ጣሪያ ውስጥ ሞቶ መጥፎ ሽታ እና ትል ሊፈጥር ይችላል። ከቺዝ ይልቅ የኦቾሎኒ ቅቤ ወይም የተቆላ ኦቾሎኒ ማድረግ አይጦችን በፍጥነት እንደሚስብ ተመልክቷል።
ተባዮቹ ተመልሰው እንዳይመጡ ለመከላከል የካርቶን ሳጥኖችን ከቤት ማስወገድ እና ምግቦችንና እህሎችን በክዳን ባላቸው ዕቃዎች ማስቀመጥ እንደሚገባ ተገልጿል። እንዲሁም ማታ ከመተኛት በፊት የሲንክ አካባቢን ማድረቅና ፍሳሽ ቀዳዳዎችን መክደን በረሮዎች ውሃ እንዳያገኙ የሚረዳ ሲሆን፣ አይጦች የሚገቡባቸውን ቀዳዳዎች ደግሞ በብረት ሽቦ ጠቅጥቆ በሲሚንቶ መድፈን አስተማማኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ መረጃ በWHO፣ CDC፣ EPA እና UC IPM የተቀናጀ የተባይ መቆጣጠሪያ መመሪያዎች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
@Addis_Reporter