በሂጃብ ምክንያት‼️
ሙስሊሙ ሰይፉን እያወዛወዘ መጥቶ ሂጇቧን ያሰረባት የሁዲ አንገት በጠሰው፤ አይሁዳዎች ተሰብስበው ሙስሊሙን ገደሉት፤ የአላህ መልእክትኛﷺ ግዙፍ ሰራዊት አዘጋጅተው አይሁዳዎች ላይ ዘመቱ።
ይህ የሆነው በነብዩﷺ ዘመን ነው።
መዲና ውስጥ ሶስት የአይሁድ ጎሳዎች ይኖሩ ነበር። “በኑ ነዲር፣ በኑ ቁረይዛ እና በኑ ቀይኑቃዕ” ናቸው።
በኑ ቀይኑቃዕ የሚባሉ ጎሳዎች ከአይሁዳዎች ይበልጥ የሀብትና የጦር መሳሪያ ያላቸው፣ የጦርነት ዕውቀት ያላቸው፣ የጠንካራ ምሽግ ባለቤትና ለእስልምናም የበለጠ ጠላትነት የነበራቸው ነበሩ።
መዲና ውስጥ ሆነው አላህና መልእክተኛው ላይ ድንበር እያለፉ፣ ሙስሊሞችና ውዱ ነብይ ላይ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ቢቆዩም ሙስሊሞች ለመመከት የሚያስችል የጠነከረ አቅም ስላልነበራቸው በዝምታ ያልፋቸዋል። ከጊዜ በኋላ የበድር ዘመቻ ተደርጎ አላህ የከሃዲያኖች አንገት ሰብሮ የሙስሊሞች አንገት ከፍ ሲያደርግ አጠቃላይ በዓረብ ደሴት የሚገኙ የእስልምና ጠላቶች ተርበተበቱ ተደናገጡ። ሙስሊሞች የትኛውም ቦታ ላይ አንገታቸው ቀና አድርገው ለመንቀሳቀስ በቁ። በኑ ቀይኑቃዖች ግን ለነበራቸው ትዕቢትና ምቀኝነት ከክፋታቸው መቆጠብ አልቻሉም።
በሂጅራ የዘመን አቆጣጠር ሁለተኛው ዓመት ላይ ነው። ሙስሊሞች የተከበረው የረመዷን ወር ሸኝተው ሸዋልን አጋምሰዋል። ታላቁ የበድር ዘመቻ ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ……
ከሙስሊሞች የሆነች አንዲት እንስት በበኑ ቀይኑቃዕ የገባያ ማዕከል እየሸጠች እየገዛች ናት። አንድ እድለ ቡስ የሆነ የሁዲ ሂጃብዋን እንድትጥል ይወተውታት ጀመረ። እሷ ግን የጌታዋን ትዕዛዝ አክብራ በእስልምናዋ ነግሳ ክብሯን የጠበቀች ንግስት ነበረችና ቦታም አልሰጠችውም። ዕቃዋን ለመሸጥ ወይም ለመግዛት አረፍ ባለችበት ሌላኛው የሁድ ከኋላ መጥቶ የላይኛው ልብሷ ከታችኛው ወይም አጠገቧ ከነበረ ነገር አሰረባት። እሷ የምታውቀው ነገር የለም። ለመሄድ አስባ ብድግ ስትል የታሰረው ልብሷ ተወጥሮ ከሰውነቷ የተወሰነው ተገለጠ። ደንግጣ ጮኸች።
የአይሁዲው ቆሻሻ ተግባር የተመለከተ አንድ ሙስሊም ሰይፉን ከሰደፉ በማውጣት እያወዛወዘው በቀጥታ ወደ የሁዲው አቀና። ከአጠገቡ ሲደርስ “እንዳንተ ያለ ቆሻሻማ ምድር መሸከም ይበቃታል” በሚል መልኩ አንገቱን በጥሶ ጣለለት። የባልደረባቸው ሞት የተመለከቱ በስፍራው የነበሩ አይሁዳዎች ተሰብስበው ሙስሊሙን ገደሉት።
ወሬው ነብዩﷺ ዘንድ ደረሰ።
የአላህ መልእክተኛ ለሰሀቦቻቸው ጥሪያቸውን አስተላለፉ። የጀግንነት ውሃ ልክ የተሞላላቸው ደማቸውና ክብራቸው ለዲናቸው ያስረከቡ አይበገሬዎቹ ሰሀባዎች ጦራቸውን አንግተው፤ ሰይፋቸውን ስለው ያቺ የምድር ኮከብ የሆነችዋን የሂጃብ ንግስት የተተናኮሉ አረመኔዎች ለመቅጣት ተሰናዱ።
በአላህ መልእክተኛﷺ መሪነት በሀምዛ ቢን ዐብዱል ሙጠሊብ ባንዲራ ያዥነት; ያ ግቡ ሳይመታ መመለሻ የሌለው፤ ትግሉ ከምድር ነስሩ ከሰማይ የሆነው የሙስሊሞች ሰራዊት ወደ በኑ ቀይኑቃዕ ጎሳ ገሰገሰ።
ለጠላት አስፈሪና አስበርጋጊ የሆነው የሙስሊሞች ሰራዊት መምጣቱን የተመለከቱ በኑ ቀይኑቃዖች በራቸው ቆላልፈው ምሽጋቸው ውስጥ መሽገው ተቀመጡ።
ስርዓት አልበኝነት የተጠናወተው ፅንፈኛው የአይሁዶች ስብስብ ለመቅጣት የመጣው የሙስሊሞች ሰራዊት ሙሉ ምሽጋቸውን በመክበብ ለድፍን አስራ አምስት (15) ቀናቶች መግባትም ይሁን መውጣት እንዳይችሉ አገቷቸው።
በአስራ አምስተኛው ቀናቸው ወደ ነብዩﷺ በማስላክ “የፈለከውን ቅጣ፣ የፈለከውን ውሰድ፣ የፈለከውን ወስን” ብለው የነብዩﷺ ፍርድ እንደ ሚቀበሉ በመግለፅ የሽንፈት ፅዋቸው በአደባባይ ተጎነጩ።
የአላህ መልእክተኛም እነዚህ ስርዓት አልባ አይሁዳዎች ሽንፈታቸው ካመኑ; ያላቸው አጠቃላይ ሀብትና መሳሪያ ወደ ሙስሊሞች ካዝና እንዲገባ እና እነርሱም ከመዲና ግዛት ተሰደው ተጠርገው እንዲወጡ ፈረዱባቸው።
ክስተቱም በታሪክ መዛግብቶች ላይ
غَزْوَةُ بَنِي قَينُقاع
የበኒ ቀይኑቃዕ ዘመቻ
ተብሎ በወፍራሙ ተፅፎ ተቀመጠ።
እንዳሳለፍነው በኑ ቀይኑቃዕ ማለት በጦርነት ላይ ብስለትና ዕውቀት ያላቸው፣ ቀስተኛና ጦረኛ ናቸው። እንደዚህ ያለን ጠላት ስትዋጋ የግድ የተወሰኑ ሰዎች መሞታቸው የታወቀ ነው። ከመሆኑም ጋ የተደፈረው የሙስሊሞች ክብርና የሂጃብ ድንጋጌ የሕይወት ዋጋ የሚከፈልለት ያህል ትልቅ ነገር በመሆኑ የአላህ መልእክተኛﷺ ውድ ሰሀቦቻቸውን ይዘው ለጦርነት ዘመቱ። ዘመቻውም በአላህ እገዛ በድል ተጠናቀቀ።።
የአንዲት ሙስሊም ክብር (ሂጃብ) በመዳፈራቸው (ለማስወለቅ በመሞከራቸው) ከሌሎች ትዕቢታቸውም ጋ ተደማምሮ ሀብት ንብረታቸው አስረክበው፣ የተዋረዱ ሆነው ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆናቸው።
እናም ወዳጄ……
ሙስሊሞች ከጠላቶቻቸው በሚደርስባቸው በደልም ይሁን ፅንፈኞች በሚያደርጉት ትንኮሳ ሰብር ሊያደርጉ ይችላሉ፤ አላህም ጊዜ ይሰጥ ይሆናል;
ጨዋታው ድንበር አልፎ ስርዓት አልበኝነቱ ከቀጠለ ግን……
ለአንዲት ሙስሊም ክብር ሲባል ምድር ከሰማይ ይደባለቃል!!
✍️ t.me/hamdquante
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio