👉ፌሮ ብረት Vs የአርማታ
[Reinforcement bar Vs Concrete mix]
🚧የኮንክሬት መዋቅር (Concrete Skeletons) የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም በአብዛኛው የተለመደው የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ያለው መዋቅር ነው።
⏺ይህ አይነቱ ስትራክቸር «Reinforced Concrete Structure ወይም ባለፌሮብረት የአርማታ ውቅር» ተብሎ ይጠራል።
⏺በመሆኑም እነዚህ ሁለት ዋና ዋና የግንባታ ግብአቶች (ፌሮ ብረት እና አርማታ) ለውቅሩ የየራሳቸው የሆነ አስፈላጊ ጥቅም አላቸው።
💫ከዚህ አንጻር፦
🚧የፌሮ ብረት (Reinforcement bar)
⏺በባህርዩ ተለጣጭ አይነት ባህርይ ስላለው በኮንክሬት ውቅሩ ላይ የሚተገበረውን ጫና (load) በቀላሉ እንዳይፈረካከስ በማድረግ እና ባለው ወጥነት የተነሳቭየተወሰነ የመለጠጥ ነጻነትን (Ductile Property) በማበልጸግ የመለጠጥ ጥንካሬን (Tensile Strength) እንዲኖረው ያደርጋል።
በዚህ አግባብ የአርማታ ውቅሩ Tension ላይ ልዩ የመቻል አቅም እንዲኖረው የሚያደርግ ግብአት ነው፡
💫አርማታ (Concrete Mix)
⏺በፌሮ ብረት መዋቅሩ ውስጥ እና ዙሪያ የሚሞላው አርማታ ደግሞ የኮንክሬት መዋቅሩ (Concrete Structure) የመኮማተር አቅም (Compressive Strength) እንዲኖረው የሚያደርግ ነው። በመሆኑም አርማታ በመዋቅሩ ላይ የሚተገበረው ጫና በአንጻራዊ ስፋት ላይ አርፎ ማዕከላዊ የፍሰት ሥርዓትን (Centerline load transfer system) ተከትሎ እንዲፈስ የሚያስችል የመድረቅ ወይም የመኮማተር ሂደትን የሚይዝ ነው።
📜ማጠቃለያ፦ አርማታ ጠንካራ የማይለጠጥ ጸባይ ስላለው ፌሮ ካልገባበት ጫና ሲበዛበት የመሰበር ወይም የመቀንጠስ አደጋ ይገጥመዋል።
⏺ፌሮ ብረትም ብቻውን ቢሆን የመለጠጥ ጸባይ ስላለው አርማታ ባይኖርበት ተጣጥፎ ይተኛል ወይም ጎብጦ ይቀራል እንጂ ራሱን ችሎ ደረቅ መዋቅር የመሆን አቅሙን አያስቀጥልም።
🌟በመሆኑም አርማታ ብቻውን ቢሆን ወይም አርማታው በዝቶ ፌሮ ብረት ካነሰ የመለጠጥ አስፈላጊ ባህርዩን ስለሚያጣ «Tensile Failure» ይገጥማል።
⏺በተቃራኒው ፌሮ ብቻውን ከሆነ ወይም ፌሮ በዝቶ አርማታ ካነሰ "Compressive Failure" ይከሰታል ማለት ነው።
⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO
@etconp