👉ስለ Field Hammer Test
🚧በአሁኑ ሰዓት ያለው የኮንክሬት ቅይጥ አተገባበር (Concrete Mixing Methodology) የተሻሻለ እየሆነ ቢመጣም አንዳድን ችግሮች ይስተዋላሉ።
🏷ለምሳሌ ያህል፦ ወጥ የሆነ የጠጠር እና የአሸዋ አይነት አለመጠቀም፣ በቤተሙከራ የቅይጥ ምጥጥን (Mix Design Ratio) ሳይወሰንላቸው የተለያዩ የሲሚንቶ ምርት አይነቶች መጠቀን፣ ሌላ ቦታ ተቀይጦ የሚመጣ እና የኮንክሬት grade ለባለቤቱ በውል ያልተገለጸ አርማታን ለሙሌት መጠቀም (ready mix concrete) የመሳሰሉት ይገኙበታል።
⏺እነዚህ ሂደቶች ለሕንጻው ወይም ለአርማታ መዋቅሩ ስትራክቸራል ፍላጎት አለመሟላት ሊያስከትል ይችላል።
⏺በመሆኑም በሳይት ላይ የምንጠቀማቸው ሙከራዎች ያሉ ሲሆን በዋናነት ሐመር ቴስት (Hammer Test) መጠቀም አለብን።
⭐️በተለምዶ የመዶሻ ሙከራ በመባል የሚታወቀው Hammer Test ኮንክሪት ከተሞላ በኋላ ባሉት በ7ኛ እና በ28ኛ ቀናት ውስጥ ሊከናወን ይችላል (በእርግጥ በመካከል ባሉ ቀናት እና ከ28ኛ ቀን በኋላም እስከ 3 ወር ድረስ የሚተገብሩ ሀገራት አሉ)።
⏺ይህ Non-Destructive Test ምድብ የሆነ የሙከራ ዘዴ የኮንክሪት ጥንካሬን የሚለካ ሲሆን ይህም ከአርማታ ውቅሩ ጥንካሬ ጋር የተያያዘ ምዘና ነው። በመሆኑም፦
❇️1ኛ) በ7ኛ ቀን፦ የ7ኛ ቀን የመዶሻ ሙከራው የአርማታው መዋቅር (Concrete Structure) ያጎለበተውን የጥንካሬ እድገት የምለካበት ሲሆን እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ከሚጠበቀው ዝቅተኛ ጥንካሬ (Minimum Compressive strength) ውስጥ ከ60% - 70% ድረስ ማጎልበት ይኖርበታል።
❇️2ኛ) በ28ኛ ቀን፦ በ28ኛ ቀን የሚደረግ ሙከራ የአርማታ ውቅሩ የሚጠበቅበትን 100% ጥንካሬ ማጎልበቱን የምናረጋግጥበት የሜዳ ሙከራ (Field Test) ነው።
⚡️ልብ ሊባል የሚገባው ይህ የሐመር ቴስት የኮንክሪት ጥንካሬን ለመወሰን ብቸኛው ዘዴ ሳይሆን እንደ ተጨማሪ ዘዴ መጠቀም የምንችለው መሆኑን ነው። ለበለጠ ውጤት ደግሞ Core Sampling፣ Cylinder test የመሳሰሉትን የጥንካሬ መፈተሻዎችን መጠቀም አለብን።
🔰የሐመር ቴስት ትግበራ ጥንቃቄ (Cautions during field Hammer test)፦
~ ቢያንስ 10 ቦታዎች ላይ መሞከርና ማንበብ
~ እያንዳንዱ ናሙና እርስ በእርሱ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ ተራራቁ መሆን አለባቸው
~ ከኮንክሬት መዋቅሩ ጠርዝ ቢያንስ 10ሴ.ሜ መራቅ
~ ሐመር ቴስት መሳሪያው የሚመታበትን አንግል ማወቅ (90° ቢሆም ይመረጣል)
~ የአሥሩን ናሙናዎች አማካኝ ማስላትና እና የመጣውን አማካኝ (Average) ውጤት ለውሳኔ መጠቀም ናቸው።
⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO
@etconp