አዲሱ መመሪያ ወደ ተግባር ሊገባ ነው
የትራንስፖርት ዘርፍ ችግሮችን ይቀርፋል የተባለው መተግበሪያ
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ መፍታትና የአሽከርካሪዎችን መንጃ ፈቃድ መቀማት የሚያስቀር አሰራር ሊተግበር መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው አዲስ አሰራር የትራፊክ ቁጥጥርን የሚያዘምንና ዜጎች የትራፊክ ቅጣት ለመክፈል የሚያጠፉትን ጊዜና የሰው ኃይል ብክነት የሚያስቀር ነው ተብሏል፡፡
ለዚሁ አገልግሎት የበለፀገው መተግበሪያ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ከተማ እስከ 400 ሰዎች ህይወት እያጠፋ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስና የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎቶችን የሚሰጠው መተግበሪያው በተሽከርካሪዎች አቅራቢያ የሚገኙ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎችን የሚጠቁምና የክፍያ ስርዓቱን በዲጂታል ዘዴዎች ማከናወን የሚያስችል ስለመሆኑም ተነግሮለታል፡፡
መተግበሪያው ወይም ሶፍትዌሩ በሀገሪቱ ብሎም በከተማዋ በማንዋል (በወረቀት) በሚተገበር የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን እንደሚያስቀርም ነው የተነገረው፡፡
ይህ መተግበሪያ ሥራውን ከአሽከርካሪና ተሽከርካር ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከኢትዮ ቴሌኮምና ከባንኮች ጋር በማስተሳሰር እንደሚሰራ ያስረዱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክበበው ሚዴቅሳ፣ ሲስተሙ ቀደም ሲል የነበረውን አሰራር በማዘመን በቁጥጥር ሂደት የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር ነው ብለዋል፡፡
=======================
@ET_SEBER_ZENA