ሰበር ዜና ET🇪🇹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot

የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ‼️
ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ቤት በነፃ‼️
ቡርኪናፋሶን በሽግግር ፕሬዝዳንትነት እየመሩ የሚገኙት ወጣቱ  ኢብራሂም ትራኦሬ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና ቤት ለሌላቸው ቡርኪናቤዎች ነፃ ቤቶችን መገንባት መጀመራቸውን አስታወቁ።
በ 2030 እያንዳንዱን የቡርኪናፋሶ ህዝብ የቤት ባለቤት ለማድረግ ራዕይ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።
እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ከደመወዝ ምንም አይነት ቀረጥ አይቀነስም ብለዋል።
ኢብራሂም በሁለት አመት የስልጣን ቆይታ ብቻ ቡርኪናፋሶን ወደ ገነት እና ከድህነት የጸዳች ሀገር እያሸጋገረ ነው ሲሉ ከበርካታ መሪዎች እና ግለሰቦች አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
ኢብራሂም ትራዎሬ ምንም አይነት የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት የለውም።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


#በምን ተቸግረዋል ??
#በእድል መወሰድ
#በረከት በማጣት
#በገንዘብ መሰለብ
#በስንፈተ ወሲብ
#በአይነጥላ
#በመተት መንፈስ
#በገብያ መዘጋት

♈#እድላቸው የተወሰደባቸው ሰዎች
♈እየሰሩ አያድጉም
♈እየደከሙ አይሳካላቸውም
♈በሄዱበት ስኬት የለም
♈አግኝቶ ማጣት
♈ለፍቶ መክሰር
♈ደክሞ መቅረት
♈ እየተመኝ አለመሳካት
♈ተወዳድሮ አለማሸነፍ
♈ተናግሮ አለመሰማት
♈ጥያቄው ተቀባይነት ማጣት
♈ስራ ተወዳድር አልፎ አለመጠራት
♈የያዘው ገንዘብ አለመበርከት
♈እያደረ መክሰር
♈ነግዶ አለማትረፍ
♈ተናግሮ አመሰማት አለማሳመን
♈በጥቅሉ  ተመኝቶ  መቅረት ይሆናል ።

#በረከት_ማጣት_በተንኮለኞች_የተሰለበው ሰው
✔ ገንዘብ ቢይዝ አይበረክትም
✔የጀመረው ነገር አይዘልቅም
✔ሲሰራውሎ ማታ ገንዘቡ አያድርም
✔ብዙ ብር ይዞ ትንሽ ብር ሲያነሳ
✔ሁሉም ብንብሎ ይጠፋል
✔የአንዳንዶቹ ይባስ ብሎ
✔ከተቀመጠበት ሳጥን ጠፍቶ ይቆያል ከኪሳችን ይጠፋል
✔እድገቱ እያደረ ቁልቁል ነው።

✅#ከሳምንት ሳምንት
#ከወር ወር
#ከአመት አመት እድገቱ እያሽቆለቆለ
#ከአበዳሪነት ወደተበዳሪነት ይወርዳል
#ባስሲል አበዳሪም ይጠፋል ጓደኛ ባድ ዘመድ ሁሉ ይጠላዋል ፊት ያዘርበታል ድህነት ላይ ይወድቃል ።

👉በዚህም ምክኒያት
✅የእድሎች ሁሉ መዘጋጋት 
✅ተስፋ መቁረጥ
✅መበሳጨት መናደድ
✅ማሰብ መጨነቅ
✅የበታችነት ስሜት መሰማት
✅የፀባይ መቀያየር ድብርት
✅የእንቅል ማጣት ስሜት
✅በሰመመን መጓዝ
✅የመርሳት ትውስታ ማጣት
✅የመሳሰሉት ችግሮች ይከሰታሉ ።
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍

#ለእድል_መወሰድ_ለበረከት_ለሰላ_መፍትሔ
#የአቱች ስር
#የዋርካ ተቀፅላ
#የሰለቢላ ስር
#የሁለ ገብስር
#የእፀ ዮዲት ስር
👉፩ #ሁሉንም በንፅህና አዘጋጅቶ አልሞ ፯ የስኳር ማንኪያ ዱቄት በነጭ ማር ለውሶ ፯ ቀን ጥዋት ጥዋት መቅመስ የተሰለበ የተወሰደ እድል ይመልሳል ያድናል

👉፪ ከዚሁ ቅመም ቀንሶ ከትኮ መያዝ ለገብያ ወሳኝነው ለሰላቢ አያስነካም

👉፫ #ለመፍት ሀብት ለገብያ ከቅመሞቹ ከትቦ ከሱቅ ከገብያ ቢያደርጉት ሀብታም ያደርጋል ገብያ ይስባል።

🌿🌿🌿🌿🌿☘☘☘☘☘☘☘
⏩ የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊታከምና ሊድን የሚችል የጤና ችግር ነው

⏩ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው የሚያሳዩአቸው ምልክቶች
🔶ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣
🔺 ፍላጎት አለመኖርን
🔶የመጨረሻው እርካታ ላይ
አለመድረስን
🔶የሌላኛውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መጨረስ
🔶ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን
🔶የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)
🔶የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)
🔶የወሲብ ጥላቻ
🔶የብልት አለመነሳት
🔶የብልት ማነስ ....

#መንስኤ እስኪት ፦ የሚጠቅመው ግንኙነት ለማድረግ በምንዘጋጅበት ወቅት
የብልት መሞትን ወይም አለመነሳትን የሚያስወግድ ነው
#መፅንኤ እስኪት ፦ የሚጠቅመው ግንኙነት በምንፈፅምበት ሰዓት ብልታችን
የሚልፈሰፈስብንን የሚያጠነክር የሚያበረታ ነው
#መፍትሄ እስኪት ፦ የሚጠቅመው በአንዳንድ ክፉ ሰዎች የክፋት ስራ
አማካኝነት በድግምት የታሰረ ብልትን የሚፈታ ማለት ነው
#ዘኢያወርድ/ ገትር ፦ ቶሎ ለሚጨርሱ ሰዎች የሚያቆይ ረዘም ላለ ጊዜ ግንኙነት እያረጉ እንዲቆይ የሚረዳ ነው
#ፀላኤ ወሲብ (ዓይነ ጥላ) ፦ የግብረ ስጋ ጥላቻ ወይም ፍራቻ ወዘተ ናቸው።
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
#የአደንድን_ፍሬ
#እፀ_ገትር
👉፩ #የአደንድን ፍሬውን አውቶ ወቅጦ አልሞ ለአምስት ቀን ቢበሉት  የመተ እስኪት ያነሳል ቅንዝር ያደርጋል
👉፪ #የእፀ ገትር ስሩን በጥርስ ቢያኝከው ብልት ያጠነክራል እንደብረት ያጠነክረዋል

✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔
✅የድግምት (የመተት መንፈስ) ዋና ተግባሩ፦
🈳ገንዘብ ማስጨረስ
🈳በረከት ማሳጣት
🈳በአጭር ጊዜ ማደህየት
🈳ከስራ ማፈናቀል
🈳በሰው ዘንድ ማስጠላት
🈳ሀገር ለሀገር ማዞር
🈳አላማን መሳት
🈳ለተለያየ በሽታ ማጋለጥ
🈳የተበላ ከሆነ ከሆድ ስራይ መስራት
🈳ሆድ መነፋት ከሆድ መገላበጥ
🈳ሆድን ወግቶ መያዝ መጮህ
🈳ማስማጥና ድርቀት መፍጠር
🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈🪈

👉 #የዓይነጥላ_መንፈስ_ዋና_አላማው
➡️የሚመጣ እድል መመለስ
➡️መልካም ነገሮችን ማበላሸት
➡️መልካሙን ትቶ ክፉውን ማሳሰብ
➡️ያለቁ ነገሮችን ማበላሸት
➡️ነገሮች ካለፉ በኋለ መፀፀት
➡️ፀባይ መቀያየር መነጫነጭ
➡️ነገሮች ጫፍ ደርሰው መበላሸት

     ☸የገርግር መንፈስ ዋና ተግባሩ የሰውን ልጅ ህይወት ባዶ ማድረግ ነው።
✳ከትዳር መገርገር
✳ከፍቅረኛ ማጣላት ማራቅ
✳ስራ ለመቀጠር መገርገር
✳ከውድድር ውጤት ማሳጣት
✳ትምህርት መገርገር ማስጠላት
✳ተምሮ ከንቱ ማድረግ
✳ከሰው ማጋጨት ማጣላት
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
     
☸ #ለመተትና_ለዓይነጥላ_መፍትሔ
#የእፀ መፍርህ ቅጠል ስር
#የጤናአዳም ቅጠል ፍሬ
#የኮሶ ቅጠል
#የእፀ መናሔ ቅርፍት
#የጭቁኝ ቅጠል

👉 #ሁሉንም በንፅህና ቀጥቅጦ አልሞ ጥዋት ጥዋት በ10 ሌትር ውሃ ዘፍዝፎ ከ7-14 ቀን ቢጠመቁት  #መተት_ዓይነጥላ_ገርግር ፈፅሞ ይጠፋል ይለቃል።

👉 #ለችግሩ ተጠቂዎች ይደርስ ዘንድ ሸር ሸር እያደረጋቹህ አጋሯቸው ለበለጠ መረጃ
0917468918
0917468918 ይደውሉልን


ትራምፕ‼️
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩኬሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በዋይት ሃውስ ላሳየው ድርጊት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃቸው እንደሚፈልጉ ብሉምበርግ አስነብቧል።
ዘለንስኪ ከዋይት ሀውስ ከወጡ በኋላ በቀጥታ ያመሩት ወደ እንግሊዝ ሲሆን 2.6 ቢሊዮን ዶላር ተበድረው ተመልሰዋል።
የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በመጪው አርብ የ100 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ድጋፍ ለማድረግ አቅዷል ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


አድዋ‼️
ከ1884-1885 ሰባት ዋና ዋና የአውሮፓ ሀገራት በንግድ ሰበብ አፍሪካን ለመቀራመት በጀርመን በርሊን/Berlin conference/ ድብቅ ውሳኔ አሳለፉ፣ማን ማንን መውረር እንዳለበት ተስማሙ።
ብዙ የአፍሪካ ሀገራት የአውሮፓውያንን ቅኝ ግዛት ተጎነጩ። የብዙ የአፍሪካ ሀገራት ባህላቸው፣ ወጋቸው፣ሀይማኖታቸው፣ ነፃነታቸው፣ታሪካቸው ጠፋ፣ተበረዘ። ቋንቋቸው ተቀየረ፣በቅኝ ግዛት ማቀቁ፣የባሪያ ንግድ ሰለባ ሆኑ፣ብዙዎች የውቅያኖስ ሲሳይ ሆኑ፣በሀገራቸው ባይተዋር ሆኑ፣እንደሰው ሳይሆን እንደ እንስሳት ተቆጠሩ፣ንብረታቸውንና ማዕዳናቸውን እራሳቸው ጭነው እራሳቸው ውቅያኖስ አቋርጠው ለአውሮፓውያን አስረከቡ።
በወቅቱ ኢትዮጵያን ለመውረር እና ቅኝ ግዛት ለመግዛት የተመደበችው ጣሊያን ግን ድል አልቀናትም፣በኢትዮጵያ ጀግኖችና ብልሃተኛ መሪዎች እና አባቶች አድዋ ላይ ተደባይቶ ተመለሰ።
የአድዋ ድል በወቅቱ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙት የአፍሪካ ሀገራት የጨለማ ውስጥ ችቦ ለኮሰ፣የነፃነት ተምሳሌት ሆነ፣የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆነ፣ኢትዮጵያም በቅኝ ግዛት ሳትገዛ፣ቋንቋዋ፣ባህሏ፣የአመጋገብ ስርዓቷ፣ሀይማኖቷ...ሳይበረዝና ሳይጠፋ በኩራት የአፍሪካ ተምሳሌት ሆነች።
አድዋ ፍቀህ የማጥለው፣ልትበርዘው የማትችለው የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ነፃነትን ለሚሹ ፍጡራን ሁሉ ተምሳሌት ነው።
"ከላይ ያስቀመጥኩት ምስል አፄ ምኒልክ መጋቢት 23 ቀን 1888 ለፈረንሳዩ ጓዳቸው የፃፉት የድል ደብዳቤ ነው።

"ጣልያን በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ ሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላክ ሀያላን ረድቶኝ ፈጀሁት። ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!"

ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን❗️
እንኳን አደረሳችሁ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የንግድ ባንክ አዲስ ህግ‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥጥሩን ጠበቅ አድርጓል‼️
ከየካቲት 17 ጀምሮ ከንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ በተላከው ደብዳቤ መሰረት የባንኩ ቴለሮች/ገንዘብ ከፋዮች/ የባንኩን ደንበኞች ተቀማጭ ቀሪ ገንዘብ መጠን ማየት እንደማይችሉ ምንጮች ገልጸዋል።
የደንበኞችን ቀሪ ሂሳብ ማየት የሚችሉት ከፍተኛ ማኔጅሮች ብቻ ናቸው።
ባንኩ ይህን እርምጃ የወሰደው እየተንሰራፋ የሄደውን የገንዘብ ማጭበርበር ለከት ለማስያዝ እንደሆነ ተጠቁሟል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ካሳቫ/Cassava‼️
ካሳቫ የተባለው ስራስር በእንጀራ ላይ ተጨምሮ እንዲሸጥ ተፈቀደ‼
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለሥልጣን ካሳቫ የተባለው ሥር በእንጀራ መልክ እንዲቀርብ መፈቀዱን አስታውቋል።

ካሳቫ የስራስር አይነት ሲሆን፤ በተለይ በደቡቡ የሀገሪቱ ከፍል ምርቱ በብዛት ይገኛል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ ስሙ ካዛቫ የተባለ ሥር  ከምግብ ምድብ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ከእንጀራ ምርት ጋር ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዲቀርብም መፈቀዱን ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህን ተገን በማድረግ ሌላ ባዕድ ነገር የሚቀላቅል ስለማይጠፋ በተቻለ አቅም  የቁጥጥር ሥራ ይሠራል ብለዋል።
የካሳቫ ተክል ከፍተኛ የካርቦሀይድሬት መጠን ያለው ሲሆን በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ነው።
ካሳቫ የስኳር በሽታን፣የልብ በሽታን እንዲሁም የህዋስ እርጅናን/cell aging/ እንደሚከላከል ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።
ካሳቫ ተክል መነሻው ከመካከለኛው አሜሪካ ሲሆን ወደ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው  በፈረንጆች 1558 በፖርቹጋሎች ሲሆን ተክሉን በማብቀል ከአፍሪካ ሀገራት ኮንኮ ቀዳሚዋ እንደሆች ታሪክ ያስረዳል። አሁን በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት በስፋት የሚመረት ሲሆን በሀገራችንም በደቡብ ኢትዮጵያ በስፋት ይመረታል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 5:29 በአዲስ አበባና በሌሎች የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ንዝረቱ ደሴ መናፈሻ፣መሃልሜዳ፣ናዝሪት፣ኮምቦልቻ አካባቢም ተሰምቶናል ብለዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.75 መመዝገቡን ዘገባዎች ያመላክታሉ።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ገዳዩ ተያዘ‼️
ብዙዎችን ያስቆጣው እና ያሳዘነው የዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ግድያ ወንጀል ፈጽሟል የተባለ ተጠርጣሪ ግለሰብ  በቁጥጥር ሥር ውሏል።
በዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሐኪም፣ ተመራማሪ፣ መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት  ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ባልታወቁ ኃይሎች መገደላቸው ይታወሳል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እሱባለው ነበረ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል። 
ወንጀል ፈጻሚው ድርጊቱን መፈጸሙን ማመኑንም ተናግረዋል። ግድያው ጥቅም ፍለጋ መኾኑን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ተመሳሳይ ወንጀሎችን ይፈጽም እንደነበርም አንስተዋል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ትራምፕ የመኖሪያ ፍቃድን በ 5 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ ሊያቀርቡ ነው‼️
ዶናልድ ትራምፕ በሀገረ አሜሪካ ለመኖር የሚያስችል የወርቅ ካርድ (Gold Card) የተሰኘ የመኖሪያ ፈቃድ $5 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ የማቅረብ ሃሳብ እንዳላቸው ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።
ከሽያጩ በሚገኘው ገቢ የበጀት ጉድለት ለመሙላት እቅድ እንደያዙ ገልጸዋል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሰሞነኛው የዋጋ ጭማሪ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር በተዳዳሚ ይስተዋላል፡፡

ሸገር ራዲዮ በተለይ ስለ ዘይት ዋጋ ማሻቀብ እና በአንዳንድ ቦታዎች ምርቱ ከገበያ የመጥፋቱ ምክንያት ምንድነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮን ጠይቋል።

እንደማሳያም 5 ሊትር #ዘይት ከሁለት ሳምንታት በፊት ሲሸጥ ከነበረው ከ1100 ንግድ 1200 በአንዴ ከ1480 እስከ 1700 ሲሸጥ ተመልክተናል፡፡

በአንዳንድ ሱቆች ደግሞ ምርቱ ስለተወደደ ከናካቴው መያዝ መተዋቸውን ነግረውናል፡፡

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች አምስት ሊትር ዘይት ከ1480 እስከ 1700 ብር፣ ሶስት ሊትር ከ850  እስከ 900 ብር፣ አንድ ሊትር ደግሞ ከ300 እስከ 350 እተሸጠ እንዳለ ነጋዴዎቹ ነግረውናል፡፡

በሁለት ሳምንት ልዩነት በምግብ ዘይት ምርት ላይ እንዲህ ያለ የዋጋ ጭማሬ ማሳየቱ ለምን ይሆን❓
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪው በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ለማወቅ ጥናት እያደረኩ ነው ብሏል።
#shegerfm
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሊፀድቅ ነው‼️
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል መመሪያ ሊጸድቅ ነው‼️

በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መመሪያው ደረጃውን የጠበቀ አሰራርን የሚከተል ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ማሟላት ያለባቸውን ደረጃዎችም ይወስናል።

በቅርቡም በባለሙያዎችና በባለድርሻ አካላት ማረጋገጫ ከተሰጠው በኋላ መመሪያው ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ42 ሺህ በላይ ምዝገባ ያጠናቀቁ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ። ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ያልተመዘገቡ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ስራ ላይ ያልዋሉ ተሽከርካሪዎች አሉ።

ይህ መመሪያ አደጋን ከመቀነስና የትራንስፖርት አገልግሎቱን የተሳለጠ ከማድረግ አንፃር ሌሎች ለአሰራር አስቸጋሪ የነበሩ ጉዳዮችን በሙሉ ለማስተካከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የፖለቲካ አሳማዎች❓❓❓
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረመስቀል ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያ ስለወደብ ጉዳይ ለምታራምደው አቋም ምላሽ ሰጥተዋል።
የማስታወቂያ ሚኒስትሩ "የፖለቲካ አሳሞች ሰሞኑን በኤሪ-ኢንፍሉዌንዛ በሽታ የተያዙ ይመስላሉ፣በየቀኑ የኤርትራ ወደብን በተመለከተ (አሰብን) የስም ማጥፋት(defamation) ዘመቻቸው ጣራ ነክቷል" ብለዋል።
የጎረቤቶቻቸውን "ወደብ እና የባህር ግዛት" ለመንጠቅ እያደረጉ ባሉት ጥንቃቄ የጎደለው ጥማት የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ አብሮ የመኖርን ደንብ ይጥሳል"ብለዋል።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


በኢትዮጵያ 65 በመቶ የሚሆኑ ተመራቂዎች ስራ ለማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው አዲስ ጥናት አመለከተ ‼️
በአፍሪካ አመራር ዩኒቨርሲቲ የተደረገው የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ከትምህርት በኋላ ወደ ስራ የሚገቡ ተማሪዎች ሁለት ሶስተኛ (65%) የሚሆኑት ከትምህርታቸው በኋላ ባለው ውስን የስራ ዕድል ላይ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ከ8,000 የሚበልጡ ተሳታፊዎችን ያሳተፈው ጥናቱ፣ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ስራ ገበታ ሲገቡ የሚገጥሟቸው ዋና ዋና ስጋቶችን የዘረዘረ ሲሆን የስራ ዕድል እጥረት (65%)፣ ምቹ ያልሆነ የኢኮኖሚ ሁኔታ (37%) እና በቂ የስራ ልምድ አለመኖር (29%) ናቸዉ።

በተጨማሪም 24% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ከምረቃ በኋላ የስራ ዕድል የማግኘት ችሎታቸው ላይ እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል ብሏል።

የ2025 የአፍሪካ የሰው ኃይል ዝግጁነት ጥናት" የተሰኘው ይህ የመጀመሪያው አህጉራዊ ጥናት፣ ስለ ከፍተኛ ትምህርት፣ ስለሙያ ዕድሎች እና ስለ ኢኮኖሚው የወጣት ተመራቂዎች እና አሰሪዎች አመለካከት ላይ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን እንደሚሰጥ ለመረዳት ችሏል።
Via Capital
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ፓስፖርት‼️
አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ‼️
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ዘርጋሁት ባለው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚስጥራዊ ህትመትና ቴክኖሎጂ ልምድ አለው ከተባለው የጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ አማካይነት ዘመኑ በደረሰበት የሚስጥራዊ ህትመት የታተመ አዲስ ፖስፖርት ዛሬ የካቲ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይፋ እያደረገ ነው፡፡
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ፀጥታ ኃይል አባላት በደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ ዓለም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በነዋሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በማለት ትናንት ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን አውግዟል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የተወሰኑ የክልሉ ፀጥታ ኃይል አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩን መዋቅሮች ለማፍረስ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው በማለት ከስሷል።

የፀጥታ ኃይሉ የአንድ ቡድን የሥልጣን መወጣጫ መሳሪያ ሊኾን እንደማይችል የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ኹኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ክልሉ ከባድ ቀውስ ውስጥ ሊገባ ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ ትናንት የተወሰኑ የፀጥታ ኃይል አባላት የቀበሌ አስተዳደሩ ማኅተሙን እንዲያስረክብ ባስገደዱበትና፣ በዚሁ ወቅት ድርጊቱን በተቃወሙ ነዋሪዎች ላይ የኃይል ርምጃ በወሰዱበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የኤርትራ መንግሥት የክተት አዋጅ‼️
የኤርትራ መንግስት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በታች የሆኑ ዜጎችን የውትድርና ስልጠና እንዲሰጥ እና እንዲለማመዱ ለሁሉም ክልሎች አስተዳደር መመሪያ ማውጣቱን ምንጮች ገልጸዋል‼️
ይህ እርምጃ ከግዳጅ የተበተኑ፣ተጠባባቂ የነበሩ እና ቀደም ሲል በማገልገል ላይ የነበሩትን ያካትታል።
በተጨማሪም ያገቡ ሴት ወታደሮች እና ልጆች ያሏቸው ወደ ወታደራዊ ክፍላቸው እንዲመለሱ ታዘዋል።
በመመሪያው መሰረት እድሜያቸው ከ50 በታች የሆኑ ግለሰቦች ከሀገር እንዳይወጡ የተከለከሉ ሲሆን ይህ የግዳጅ ምልመላ እና በእንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። የክልል አስተዳደሮች የሚመለከታቸውን ዜጎች የማሳወቅ፣ የመመዝገብ እና የማሰባሰብ ስራ መጀመራቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ጦርነቱ ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለሚገመት ይህ ድንገተኛ እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ቅስቀሳ በኤርትራ ማህበረሰብ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ "የኤርትራ መንግሥት የፕርቶሪያ ስምምነትን ያልተቀበሉ ሰዎችን በማሳተፍ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው" የሚል ሀሳብ ለአልጀዚራ እንግሊዘኛው ክፍል በኩል ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።
ይህን መረጃ የወሰደው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ከሚሰራ ከአንድ ትልቅ አለም አቀፍ ግበረሰናይ ድርጅት/ ከኤርትራ ቅርንጫፍ ነው።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሰበር መረጃ‼️
በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር ተናገሩ‼️
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእጅጉ እየጣሰች ነው ብለዋል።  በቅርቡ በግብፅ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ በዛሬው እለት ዝተዋል።

አክለው የተናገሩት በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር ግብፅ ኢንተርኔቱን እና ሶሻል ሚዲያውን በግብፅ ጦር ምስሎች አጥለቅልቃው እየተመለከትን ነው ሲሉ ከሰዋል።
በግብፅ በኩል ያልተለመደ የተባለለት ሰሞንኛ ክስተት የተስተዋለው በተለይም የግብፅ ፓራትሮፐር ብርጌዶች በኦክቶበር 7 ሐማስ ጥቅም ላይ ያዋለውን  አይነት የአውሮፕላን ዝላዮች እና ኦፕሬሽኖችን ጨምሮ የተቀናጀ ነው የተባለለትን የወታደራዊ ስልጠና ልምምዶችን የሚያካሂዱበት ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መዳረሱን ተከትሎ ነው።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሳፋሪኮም‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በጥቂት አከባቢዎች ተቋርጦ የነበረው አገልግሎታችን ወደነበረበት ተመልሷል ሲል ሳፋሪኮም አስታወቀ። ስለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ ጠይቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ታገደ‼️
የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በ AI technology ዘርፍ ብዙዎችን ያስደመመውን Deep seek የተባለውን መተግበሪያ ቁልፍ አድራሻዎችን፣የግለሰብ መረጃዎችን በመስረቅ እና አሳልፎ በመስጠት ጠርጥሬዋለሁ ያለች ሲሆን የወንጀል ምርመራ እስኪደረግ ድረስ DeepSeek የተባለው መተግበሪያ በሀገሪቱ እንዳይሰራ ማገዷን አስታውቃለች።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA

20 last posts shown.