ገንዘብ ደስታን አይገዛም የሚሉ ሰዎችን ጆሮ አትስጧቸው። በገንዘብ የት እና እንዴት ገዝታን መሸመት እንዳለባቸው ስለማያውቁ ነው። ደስታ ዕቃ አይደለም ከሱቅ አይገዛም። የደስታ ምንጩ ብዙ ነው። የወላጆችህን የህክምና ወጪ መሸፈን ደስታን ይሰጣል። የወንድም እህቶችህን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት ደስታን ያጎናፅፋል። በዙሪያችን ያሉትን የተቸገሩ ሰዎች መርዳት ሀሴት ያላብሳል።
ሰነፎች መስራት ስለማይወዱ ድህነትን አቅፈው ስለ ገንዘብ መጥፎነት ይለፍፋሉ። ሕይወታቸውን ለመቀየር እዚህ ግባ የሚባል ትግል ሳያደርጉ የስራ ሰዎችን ይንቃሉ። ትጉህ የስራ ሰዎችን በአሉባልታ ስም ያጠለሻሉ። እነሱ ያውሩ የኛ ድርሻ ጠንክሮ መስራት ነው።
ገንዘብ ይኑራችሁ። አብዘኻኛው ችግሮቻችን በሳቢ የሚቀረፉ ናቸው። ወጣትነታችንን እንዳይባክን። እየተወራረሰ የመጣው የድህነት ሰንሰለት እኛ ላይ ሊበጠስ ይገባዋል። Have a great Day!
Share:
@ETHIO_SIGMA_ET