❗️ጓደኛን ስትመርጥ . . . ❗️
📌አመለካከትህ የምትመርጠውን ጓደኛ ይወስናል፤ አብረህ የምትከርመው ጓደኛ ደግሞ በተራው አመለካከትህን የመወሰን ጉልበት ስላለው ወደ ሕይወትህ ዘልቆ እንዲገባ የምትፈቅድለትን ሰው በጥንቃቄ ምረጥ፡፡
📌“ጓደኝነት እንደ ሊፍት (Lift / Elevator) ነው፡፡ ወይ ወደላይ ያወጣሃል ወይም ደግሞ ወደታች ያወርድሃል” የሚል አባባል አለ፡፡ ሌላ ረዘም ላለ ጊዜ የከረመ አባባል፣ “በአጠገብህ የሚገኙ የአምስቱ ቅርብ ጓደኞችህ ጭማቂ ነህ” ይላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ልቦናን የሚያነቃ እውነት ይዘዋል፡፡ የቅርብ ጓደኞችህን የያዝክበት የራስህ የሆነ ምክንያት ቢኖርህም፣ ለውጥ ለማምጣት በምትፈልግበት ጊዜ በዙሪያህ የሚገኙት ሰዎች ምን አይነት ሰዎች አንደሆኑ ማሰብ መጀመርህ አይቀርም፡፡
📌ከዚህ በታች ጓደኛን ስትመርጥ ሊኖርህ ስለሚገባ የምርጫ መመዘኛ የሚያስተምሩ ነጥቦችን ታገኛለህ፡፡
1. “ወደ ላይ” ምረጥ፡- የማደግና የመሻሻል ፍላጎቱ ካለህ የምትይዛቸው ጓደኞች ከአንተ ከፍ ያሉ እንዲሆኑ ትመከራለህ፡፡ ከፍ ያሉ ሰዎች ከፍ ያደርጉሃል፡፡ የበሰሉ ሰዎች ብስለትን ያስተዋውቁሃል፡፡ ይህንኑ ተመሳሳይ መርህ በመከተል የአንተን ላቅ ያለ ደረጃ ፍለጋ አንተን የሚቀርቡህ ሰዎች የመኖራቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንተ ግን ወደ ላይ መመልከትህን መዘንጋት የለብህም፡፡
2. ተመሳሳይ መርህ ያለውን ምረጥ፡- በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት ሳንክድ፣ አመለካከትንና መርህን አስመልክቶ ግን ተመሳሳይነት ያላቸውን ሰዎች መቅረብ ስኬታማ ያደርግሃል፡፡ መርህን አስመልክቶ ልዩነታችሁ ከጎላ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መያዝ፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ልዩነትን በማስታረቅ ዙሪያ የሚሽከረከር ግንኙነት ውስጥ እንድትቀር ያደርግሃል፡፡
3. ተመሳሳይ ግብ ያለውን ምረጥ፡- የዚህ ምርጫ ጥቅሙ የመደጋገፍና የመበረታታት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንተ ያለህ ግብ ሕብረተሰብህን የማገልገል ከሆነና የቀረብከው ጓደኛ ዋና ግቡ በገንዘብ የመበልጸግ ብቻ ከሆነ የጋራ የሆነን ሃሳብ በመወያየት የሞራልና የተግባር ድጋፍ መለዋወጥ ሊያስቸግራችሁ ይችላል፡፡
4. በስኬትህ ደስ የሚለውን ምረጥ፡- በተሳካልህ ቁጥር ከአንተ ጥቅምን እንደሚፈልግ የሚያሳይ፣ ስለስኬትህ ስትነግረው ብዙም ሃሳብ የማይሰጥ፣ ስኬትህን አስምልክቶ ከአንተ ጀርባ ለሌሎች የሚያወራና የመሳሰሉት ባህሪይ የሚያንጸባርቅን ሰው ጓደኛ ከማድረግህ በፊት ደግመህ ልታስብበት ይገባል፡፡
5. በውድቀትና በችግር የማይለይህን ምረጥ፡- ሁሉም ነገር በተሟላልህ ወቅት አብሮህ ሆኖ፣ ሁኔታዎች እንደ ቀድሞው አልሆን ሲሉህና ነገሮች ሲፈራርሱብህ ከአንተ ዘወር የሚል ባህሪይ ያለበት ሰው አይበጅህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ከአንተ ከሚያገኙት ጥቅም አንጻር ብቻ የሚቀርቡህ ናቸውና ስሜትህን ጠብቅ፡፡
6. እውነቱን የሚነግርህን ምረጥ፡- እውነቱን የማይነግርህ ሰው ከምታይበት ባህሪ አንዱ አንተ ጋር ሲሆን አንተን ደስ የሚልህን ብቻ እየመረጠ የመንገር ሁኔታ ነው፡፡ እውነተኛ ወዳጅ ግን እየወደደህና እያከበረህ፣ ቢያምህም እውነቱን ይነግርሃል፡፡ ይህ አይነቱ ሰው ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም፡፡
7. ማንነትህን የሚቀበልን ምረጥ፡-- ስህተትህን ሳይደብቅ እውነቱን እየነገረህ፣ ነገር ግን ማንነትህን ከነስህተትህና ከነጉድለትህ የሚቀበልን ሰው ማግኘት ታላቅ እድል ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን ሰው ካገኘህ ለጓደኝነት አትለፈው፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ባወቀህ መጠን አይንቅህም፤ እንዲያውም በወዳጅነቱ እየተመቻቸ ይሄዳል፡፡ በተጨማሪ፣ እውነተኛ ወዳጅ ዘርህን፣ መልክና ቁመናህን፣ እንዲሁም ሁለንተናህን የሚቀበል ሰው መሆኑን አትዘንጋ፡፡
8. መስመርህን የሚያከብርን ምረጥ፡- ጨዋ ጓደኛ መሆንና ማድረግ የማትፈልገውን ያከብራል፤ የግል ሕይወትህን አስመልክቶ የፈቀድክለት ድረስ ነው የሚገባው፡፡ በአንተ ህይወት መብተኝነት አይሰማውም፡፡ የሚበጅህ ጓደኛ፣ ጓደኝነት ማለት በየቀኑ መገናኘት፣ አብሮ ውሎ አብሮ ማደር፣ አብሮ መላስና መቅመስ እንዳልሆነ በሚገባ ያውቃል፡፡ ሌላ ማሕበራዊና ግላዊ ህይወት እንዳለህም በማወቅ ለቀቅ ያደርግሃል፡፡ ልቡ ግን ሁል ጊዜ ከአንተ ጋር ነው፡፡
9. ድብቅ ያልሆነውን ምረጥ፡- ማን እንደሆነ፣ ምን እንደሚያደርግ፣ ከየት እንደሚመጣና ወደ የት እንደሚሄድ በቅጡ የማይታውቀውን ሰው ከመወዳጀት ቆጠብ ማለት ይበጅሃል፡፡ ጓደኛ ሊታይ፣ ሊደመጥ፣ ሊዳሰስ ይገባዋል፡፡ በተለያዩ የማሕበራዊ የመገናኛ መረቦች ላይ “በስም” እና “በፎቶ” ለተዋወከው ሰው ሁሉ ልቦናንና ስሜትን መክፈት ከመስመር ያወጣሃል፣ አልፎም የስሜት ቁስል መሆኑ አይቀርም፡፡
💫 Share with your Friends💫
🙌Post በምናደርጋቸው React አድርጉ😊
@Elshio_Academy
@Ethio_students_Only