ብሄራዊ ባንክ የሚያወጣው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ‹‹ግልፅነት ይጎድለዋል›› ሲሉ የባንክ ሀላፊዎች ተናገሩ፡፡
ብሄራዊ ባንክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎችን ማውጣት የጀመረ ሲሆን በጨረታው አሰራር ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ባንኮች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡
አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የባንክ አመራር ሲናገሩ ‹‹እኛ ያቀረብነው ዋጋ ተቀባይነት እንዳላገኘ ብቻ ነው የሚገለፅልን›› ብለዋል፡፡ እንዳስረዱትም የመጫረቻ ዋጋቸውን በኢሜይል እንዲልኩ የሚደረግ ሲሆን ‹‹ጨረታውን ማን እንደሚከፍተው እንኳ አናውቅም›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹የእኛ ዋጋ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ያለውን ልዩነትም የምናውቅበት ምንም መንገድ የለም›› ካሉ በኋላ የጨረታው አሰራር ግልፅነት እንደሚጎድለው አስረድተዋል፡፡ አንድ ሌላ የባንክ ሀላፊ እንደገለፁት ደግሞ እነሱ ያቀረቡት ዋጋ ከሌሎች አነስተኛ ተብሎ ውድቅ ቢደረግም በሶስተኛው ዙር ጨረታ ወቅት ያቀረቡት ዋጋ ግን ከአማካኙ የበለጠ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡
የባንክ ሀላፊዎቹ እንደሚሉት ብሄራዊ ባንክ በሚያወጣቸው ጨረታዎች የሚገልፀው በአማካኝ የቀረበለትን ዋጋና የተወዳደሩትን ባንኮች ብዛት ብቻ ነው፡፡
ምን ያህል ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን እንዳገኙና ምን ያህሉ እንዳጡ የሚገልፀው ነገር እንደሌለም አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም በቀጣይነት ብሄራዊ ባንኩ በሚያወጣቸው ጨረታዎች ላይ ግልፅነት ያለው አሰራር እንዲከተል አሳስበዋል፡፡
ብሄራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ እንዲህ አይነት ጨረታዎችን እንደሚያወጣ ያስታወቀ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ለአራተኛ ጊዜ ጨረታውን ማከናወኑ ይታወቃል፡፡
በአራተኛው ዙር ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር ቀርቦ በአማካኝ በ131 ብር ከ49 ሳንቲም ለመሸጥ መቻሉን ይፋ ማድረጉን መግለፃችን ይታወሳል፡፡
@Ethio_fastnews🤩