ኢትዮ ፈጣን ዜና - Ethio Fast News 🇪🇹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Sport


የሀገር ውስጥ እና ውጪ ዜናዎችን በፍጥነት እና በጥራት የሚያገኙበት ቻናል
Ethiopian Fast news 24/7

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Sport
Statistics
Posts filter


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የትምህርት ሚኒስቴር እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሊሰጡ ነው ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዲዘጋ የሚያደርገውን ትዕዛዝ በፊርማቸው ሊያፀድቁ መሆኑን እየተነገረ ነው።

የትምህርት እና የሲቪክ መብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ዴሞክራት ፓርቲን የወከሉ እንደራሴዎች ትዕዛዙ የሀገሪቱን የትምህርት ሥርዓት ለማፈራረስ ያለመ ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ስለመሆኑም ተነግሯል።

የጥቁሮች መብት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ‘NAACP’ የተባለ ተቋም ፕሬዚዳንት ዴሪክ ጆንሰን፣ “የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በፌዴራል መንግሥት ድጎማ ላይ ጥገኛ ለሆኑ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ሕፃናት የዛሬ ቀን ጨለማ ቀን ነው” ብለዋል።

የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተር ፓቲ ሙሬይ በበኩላቸው፣ “ትራምፕ እና ኢሎን መስክ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማፍረስ የማይሆን ጨዋታ እየተጫወቱ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ግማሽ የሰው ኃይል እያባረሩ ነው” ሲሉ ተችተዋል።

የሀገሪቱ ብሔራዊ የወላጆች ኅብረት ደግሞ “እየተደረገ ያለው የትምህርት ሥርዓቱን ማስተካከል ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት የሚገባቸውን ነገር እንዳያገኙ የማድረግ እንቅስቃሴ ነው፤ እኛ ግን ይህ እንዲሆን በፍፁም አንፈቅድም” ብሏል።

እንደ ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ ትራምፕ የሚፈርሙት ትዕዛዝ የትምህርት ሚኒስትሯ ሊንዳ ማክማሆን የትምህርት ሚኒስቴሩ እንዲዘጋ አስፈላጊውን ሒደት እዲያመቻቹ እና ሥልጣኑን ለግዛቶች አንዲያስተላልፉ ያዝዛል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የትምህርት ሚኒስቴሩን አባካኝ እና በሊበራል ርዕዮተ ዓለም የተበከለ ነው ብለው እንደሚያስቡ አልጀዚራ ዘግቧል።

@Ethio_fastnews🤩
@Ethio_fastnews🤩


የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መጋቢት 13/2017 ዓ.ም)

@Ethio_fastnews🤩
@Ethio_fastnews🤩


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች !

🌍በአፍሪካ ሀገራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ🌍

01:00 |🇹🇬 ቶጎ ከ ሞሪታንያ 🇲🇷
04:00 |🇸🇩 ሱዳን ከ ሴኔጋል 🇸🇳

🌍በአውሮፓ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ 🇪🇺

11:00 |🇱🇮 ሌችተነስቴን ከ ሰሜን መቆዶኒያ 🇲🇰
02:00 |😀 ሞልዶቫ ከ ኖርዌይ 🇳🇴
02:00 |🇲🇪 ሞንቴኔግሮ ከ ጊብራላታር 😀
04:45 |🇮🇱 እስራኤል ከ ኢስቶኒያ 😀
04:45 |🏴󠁧󠁢󠁷󠁬󠁳󠁿 ዌልስ ከ ካዛኪስታን 😀
04:45 |🇨🇿 ቼክ ሪፐብሊክ ከ አይስላንድ 🇮🇸

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት !

🌍በአፍሪካ ሀገራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ 🌍

🇧🇼 ቦስትዋና 1-3 አልጄሪያ 🇩🇿
🇬🇶 ኢኳቶሪያል ጊኒ 2-0 ሳኦ ቶሜ 🇸🇹
🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ ጅቡቲ 🇩🇯
🇨🇩 ኮንጎ 1-0 ደቡብ ሱዳን 🇸🇩
🇷🇼 ሩዋንዳ 0-2 ናይጄሪያ 🇳🇬
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 2-0 ሌሶቶ 🇱🇸
🇧🇮 ብሩንዲ 0-1 አይቮሪኮስት 🇨🇮
🇬🇭 ጋና 5-0 ቻድ 🇹🇩
🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-2 ግብፅ 🇪🇬
🇰🇲 ኮሞሮስ 0-3 ማሊ 🇲🇱
🇬🇳 ጊኒ 0-0 ሶማሊያ 🇸🇴
🇳🇪 ኒጄር 1-2 ሞሮኮ 🇲🇦

🌍በአውሮፓ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ 🇪🇺

😀 ቆፕሩስ 2-0 ሳን ማሪኖ 😀
🇦🇩 አንዶራ 0-1 ላቲቪያ 🇱🇻
እንግሊዝ 2-0 አልባኒያ 🇦🇱
🇲🇹 ማልታ 0-1 ፊንላንድ 🇫🇮
🇵🇱 ፖላንድ 1-0 ሊቴኒያ 😀
🇷🇴 ሮማኒያ 0-1 ቦስኒያ 🇧🇦

የተቆጠሩ ጎሎችን ለመመልከት

@perfect_sport_et_highlight1

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍 በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (አፍሪካ)🌍

               ⏰ተጠናቀቀ

🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-➋ ግብፅ 😀
                        🥅ሳላህ
                        🥅ዚዞ

🇬🇳 ጊኒ 0-0 ሶማሊያ 🇸🇴

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍 በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (አፍሪካ)🌍

               ⏰እረፍት

🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-➋ ግብፅ 😀
🥅ሳላህ
🥅ዚዞ

🇬🇳 ጊኒ 0-0 ሶማሊያ 🇸🇴

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (በአውሮፓ) 🇪🇺

               ⏰ተጠናቀቀ

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 እንግሊዝ ➋-0 አልባኒያ 😀
🥅ሉዊስ ስኬሊ
🥅ሀሪ ኬን

😀 አንዶራ 0-➊ ላቲቪያ 🇱🇻
                     🥅ዳሪዮ ሲትስ

😀 ፖላንድ ➊-0 ሊቱአኒያ 😀
🥅ሊዋንዶስኪ

😀 ማልታ 0-➊ ፊንላንድ 😀
                     🥅ኦሊቨር አንትማን

😀 ሮማንያ 0-➊ ቦስንያ 😀
                     🥅አርሚን ጊጎቪች

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍 በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (አፍሪካ)🌍

⏰01'

🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-0 ግብፅ 😀

🇬🇳 ጊኒ 0-0 ሶማሊያ 🇸🇴

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
የጨዋታ አሰላለፍ

06:00|🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ ግብፅ 😀

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (በአውሮፓ) 🇪🇺

               ⏰እረፍት

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 እንግሊዝ ➊-0 አልባኒያ 😀
🥅ሉዊስ ስኬሊ

😀 አንዶራ 0-0 ላቲቪያ 🇱🇻

😀 ፖላንድ 0-0 ሊቱአኒያ 😀

😀 ማልታ 0-➊ ፊንላንድ 😀
                     🥅ኦሊቨር አንትማን

😀 ሮማንያ 0-➊ ቦስንያ 😀
                     🥅አርሚን ጊጎቪች

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (በአውሮፓ) 🇪🇺

⏰01'

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿እንግሊዝ 0-0 አልባኒያ 😀

😀 አንዶራ 0-0 ላቲቪያ 🇱🇻

😀 ፖላንድ 0-0 ሊቱአኒያ 😀

😀 ማልታ 0-0 ፊንላንድ 😀

😀 ሮማንያ 0-0 ቦስንያ 😀

@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


የUAEው ሚዲያ ስራ አቋረጠ።

መቀመጫውን የተባበሩት ዓረብ ኤሜሬትስ (UAE) አቡ ዳቢ ያደረገው አል አይን ኒውስ (Al Ain) ዲጂታል ሚዲያ የአማርኛ የአገልግሎቱን አቋርጧል።

የ2015 (እ.ኤ.አ) የተቋቋመውና ከ " ዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙሃን ኢንቬስትመንት ፍሪ ዞን ኤል.ኤል.ሲ " ኩባንያ የንግድ ምልክቶች አንዱ የሆነው አል አይን ኒውስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በይፋ ባይታወቅም ከትላንት በስቲያ አንስቶ የአማርኛ አገልግሎት አቁሟል።

የዲጂታል ሚዲያው ቢሮውን ዘግቶ ከኢትዮጵያ ጠቅላሎ ሊወጣ እንደሆነም ተሰምቷል።

አል አይን አማርኛ ባለፉት ዓመት በአብዛኛው የተለያዩ ሀገራት የውጭ ሀገራት መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

ሚዲያው አገልግሎቱን ስላቆመበት ምክንያት ተጨማሪ መረጀ ካለ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


Forward from: PERFECT ስፖርት በኢትዮጵያ™
🌍 በአለም ዋንጫ ማጣሪያ (አፍሪካ)🌍

⏰የጨዋታ ውጤት

🇰🇲 ኮሞሮስ 0-❸ ማሊ 🇲🇱
🇬🇶 ኢኮቶሪያል ጊኒ ➋-0 ሳኦ ቶሜ 🇸🇹
🇧🇼 ቦትስዋና ➊-❸ አልጄሪያ 🇩🇿
🇧🇫 ቡርኪናፋሶ ➍-➊ ጅቡቲ 🇩🇯
🇨🇩 RD ኮንጎ ➊-0 ደቡብ ሱዳን 🇸🇩
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ ➋-0 ሌሴቶ 🇱🇸
🇷🇼 ሩዋንዳ 0-➋ ናይጄሪያ 🇳🇬

🌍የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ (በአውሮፓ) 🇪🇺

🇨🇾 ሳይፕረስ ➋-0 ሳን ማሪኖ san 🇸🇲


@Perfect_sport_et
@Perfect_sport_et


➡️ የሕንጻ የፊተኛው ገጽ መብራት ወይም የፋሳድ ላይት መብራት ያለመስቀል እና/ወይም ያለማብራት 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ የንግድ ተቋሙ መግቢያ በር ዝግ ሆኖ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ ክፍት መሆኑን የሚያመለክት በኤሌክትሪክ የሚሰራ ምልክት ያለማድረግ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ከምሽቱ 4፡00 በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጥ ፣ መውጣት ወይም የስምሪትን መስመር ማቆራረጥ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ የከተማ አስተዳደሩ ካወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፊ በላይ ተሳፋሪውን ማስከፈል 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።

ከገንዘብ እና አስተዳደራዊ ቅጣቶች በፊት ከምሽት 3:30 በፊት የንግድ ተቋሙን ዘግቶ የተገኘ ነጋዴ የ24 ሰዓት የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንደሚሰጠው አቶ ሙሰማ ጀማል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

(ደንቡ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆነው ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ሲወጣለት ሲሆን አሁን ላይ የመመሪያው እየተዘጋጀ ይገኛል)

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


በመጀመሪያ ደረጃ በሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ላይ የማይታረሙ የንግድ ተቋማት ላይ እስከ መጨረሻው የገንዘብ እርከን ከተቀጡ በኋላ የንግድ ፈቃድን እስከ መሰረዝ የሚደርስ ቅጣት እንዲቀጡ ይደረጋል።

ይህ ከመሆኑ በፊት ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ በሁሉም ሚዲያዎች ይሰራል።

ደንቡን ተግባራዊ አድርገናል እዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖረውም የማስተዋወቁ ስራ ግን በሰፊው ይሰራበታል የቅጣት እርከኖቹን ይፋ ማድረግ ጀምረናል።

ደንቡ ዝርዝር መመሪያ በቢሮው እየተዘጋጀለት ነው በፍጥነት ጨርሰን ግልጽ እናረጋለን።

ህጉ የሚሰራው የኮሪደር ልማቱ ያለባቸውን አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን በመላው አዲስ አበባ በ 11 ንዱም ክፍለ ከተሞች ዋና ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ ሁሉንም የንግድ ተቋማትን ላይ ነው።

የትራንስፖርት እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሁሉንም የግል የትራንስፖርት ሰጪ አካላትን ጨምሮ የሚመለከት ነው ይህንንም መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር በመሆን በጋራ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።

አስተዳደራዊ የመጀመሪያ ደረጃ የገንዘብ ቅጣት እርከን ምን ይመስላል ?

➡️ ከምሽቱ 3፡30 በፊት የንግድ ተቋሙን መዝጋት 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ለተገልጋይ ሊያቀርብ የሚችለው አገልግሎት ወይም ምርት እያለው የለም በማለት ተገልጋይ እንዳይስተናገድ ማድረግ 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ መንገድ ዳር ያሉ ንግድ ተቋማት እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከምሽት እስከ ንጋት ድረስ የተቋሙን የውጭ እና የውስጥ መብራት አለማብራት 7 ሺህ ብር ያስቀጣል።

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews


" የገንዘብ ቅጣቱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥፋት ፣ሁለተኛ ደረጃ ጥፋት እያለ እስከ አምስተኛ ደረጃ የሚያስቀምጣቸው የቅጣት እርከኖች አሉት " - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደምብ 185/2017 የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ምሽት 4 ሰዓት ድረስ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ተቋማት ደግሞ ምሽት 3:30 ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከመጋቢት 10 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ደንቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያጸደቀው የካቲት 29/2017 ዓ/ም የነበረ ሲሆን ይህ ደንብ መመሪያዎች ተዘጋጅተውለት ከመጋቢት 10/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

የንግድ ቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል ደንቡ የህግ ተጠያቂነትን ጨምሮ ፣የገንዘብ እና በመጨረሻም ንግድ ፈቃድን እስከ መሰረዝ የሚደርሱ ቅጣቶች እንዳሉት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ/?

" የገንዘብ ቅጣቱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥፋት ፣ሁለተኛ ደረጃ ጥፋት እያለ እስከ አምስተኛ ደረጃ የሚያስቀምጣቸው የገንዘብ ቅጣት እርከኖች አሉት።

@Ethio_fastnews
@Ethio_fastnews



17 last posts shown.