ብሪክስ የአሜሪካን ዶላርን የሚተካ የክፍያ ሥርዓት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተነገረ
የብሪክስ አባል ሀገራት በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የአሜሪካን ዶላር የበላይነትን ለመገዳደር አዲስ የክፍያ ሥርዓት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት ይህ አዲስ የክፍያ ዘዴ ከባህላዊው ሥርዓት ፈጽሞ የተለየ ሲሆን በአለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
በተለይም የአሜሪካ ዶላር በአለም አቀፍ የንግድ ልውውጦች ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረውና አብዛኛዎቹ የንግድ ስምምነቶች በአባል ሀገራቱ የገንዘብ ምንዛሬዎች እንደሚፈጸሙ ይጠበቃል።
ሚኒስትሩ አክለውም ይህ አዲስ የክፍያ ሥርዓት ከብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ላሉ ሀገራትም ክፍት እንደሚሆን አረጋግጠዋል። ይህም ማለት ማንኛውም ሀገር የአሜሪካን ዶላር ሳይጠቀም የንግድ ልውውጦችን ማከናወን ይችላል ማለት ነው።
በተጨማሪም ይህ አዲስ የክፍያ ሥርዓት በአሜሪካና በአውሮፓ ቁጥጥር ሥር ባለው የ ስዊፍት የክፍያ ሥርዓት ላይ እንደማይመሰረትና ይልቁንም ከውጭ ተጽዕኖ ነፃ የሆነ የራሳቸውን የክፍያ መድረክ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
@Ethio_fastnews🤩