አቶ ታምራት ላይኔ የዓለም አቀፍ የብሎክቼይን አስተዳደር አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ታምራት ላይኔ አድማሱን የሾማቸው ኩላዳኦ የተሰኘው የክሪፕቶ ከረንሲ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱ አቶ ታምራትን ለምን እንደመረጣቸው ሲገልፅ ኢትዮጵያ ከአምባገነን መንግስት ወደዲሞክራሲ በምትሸጋገርበት ወቅት የተቋማት ግንባታና እርቀ ሰላም ላይ ትልቅ ሚና በመጫወታቸው እንደሆነ አስረድቷል፡፡
ከዚህ ልምዳቸው በመነሳት አሁን ደግሞ ድርጅቱ እያደገ በመጣው አዲሱ የክሪፕቶ ገበያ በመንግስታት ውስጥ ለመስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ያግዛሉ የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡
አቶ ታምራት ላይኔ ሹመቱን ከተቀበሉ በኋላ ሲናገሩ ‹‹አስተዳዳራዊ ውድቀቶች እምነትን መልሶ በመገንባት ስራ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳላቸው የመጀመሪያ የአይን ምስክር ነኝ፡፡ ኩላ ዳኦ የአለማችን የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ ባልሆነበት በዚህ ዘመን ይህን ለማስተካከል የሚጥር ድርጅት በመሆኑ አብሬው ለመስራት ወስኛለሁ›› ብለዋል፡፡
ድርጅቱ በክሪፕቶ ከረንሲ አማካኝነት የተለያዩ የልማትና የእርዳታ ስራዎችን የሚያከናውን እንደሆነ በድረ ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡
@Ethio_fastnews🤩