"የተደረገው የስልጣን ሽግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በተገኙበት በትግራይ መቐለ ቢሆን ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር" ጌታቸው
አቶ ጌታቸው ረዳ በመቀሌ ከጄኔራል ታደሰ ወረደ የቀረበላቸውን የምስጋናና የሽኝት መርሐግብር ግብዣ ውድቅ አደረጉ
የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው ረዳ የሹመት ስልጣናቸውን ካገኙ በኃላ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።
ሚንስትሩ UMD ለተባለ ሚድያ በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ "በትግራይ የተደረገው የስልጣን ሽግግር የትግራይ ህዝብን ደህንነትና ህልውና የሚያስጠብቅ አይደለም" ብለውታል።
የኢፌዱሪ ጠቅላይ ሚንስትር ለድህንነታቸው ያደረጉትን ጥንቃቄ እውቅና በመስጠት ያመሰገኑት አቶ ጌታቸው፤ በማንኛውም መመዘኛ የትግራይ ህዝብ መልሶ ወደ ጦርነት እንዳይገባ የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከጫፍ እንዲደርስ አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀው "በትግራይ ክልል የተጀመረው የለውጥ ፍላጎት ወደ ኋላ የሚጎትት ማንኛውም እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም፤ አይሳካም" ብለዋል።
ትግራይ ላይ እሳቸውን ለመግደል የተሸረበ ሴራ እንደነበር፤ ይህንንም ሸሽተው ከትግራይ ፓለቲካ የመውጣት አንዳች ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
"የተደረገው የስልጣን ሽግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በተገኙበት በትግራይ መቐለ ቢሆን ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ "ትላንትን እየመዘዙ ቁርሾና ቂም በቀል ማቀጣጠል ፋይዳ የለውም" በማለት ተናግረዋል።
"እኔን በክብር መሸኘት ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠው በትግራይ ክልል የሰፈነው ህግ አልባ አካሄድ እንዲስተካከል መስራት ነው" ሲሉ አክለዋል።
"የትግራይ ህዝብ የሰጠኝ ክብርና እውቅና ከፍተኛ ነው፤ ከዚህ ክብርና እውቅና በላይ የምመኘው የምስጋና መድረክ የለም" ሲሉ የገለፁ ሲሆን፤ በአዲሱ የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር የቀረበላቸውን የምስጋናና የክብር የሸኝት ፕሮግራም እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።
በክልሉ ያሉ ሌቦችና ህገወጦች አደብ ለማስገዛት ለሚደረገው ጥረት እንደሚያግዙ ህዝቡ ለማገለገል እንደ ትናንት ዛሬም ዝግጁ እንደሆኑም ገልፀዋል
@Ethio_fastnews🤩