ለኮሪደር ልማት አገልግሎት ላይ የዋሉ መብራቶችን የሰረቀው ተከሳሽ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
ወንጀሉ የተፈጸመው የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 8:00 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዋሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን በኮሪደር ልማት ላይ የተገጠሙ መብራቶችን ቆርጦና ነቅሎ በመውሰድ ሊያመልጥ ሲል በወቅቱ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።
ተከሳሽ ላይም ተገቢው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማደራጀት ምርመራ ተጣርቶበት በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፤
የተከሳሽን መዝገብ የተከታተለው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ተከሳሽን ያርማል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስተምራል በማለት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል። (ዳጉ_ጆርናል)
@Ethionews433 @Ethionews433