ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ።
ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ስድስት ተከሳሾች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል በሚል የቀረበባቸው ክስ ላይ የወንጀል ድርጊት እንዳልፈጸሙ ጠቅሰው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ዛሬ ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ከአንድ ወር በፊት አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ ወንጀል ክስ እንዲሁም በ1ኛ ተከሳሽ ብቻ ደግሞ የአየር መንገዱን መልካም ስም ለሚያጎድፍ በተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒውተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።
ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ዝርዝር የተገለጸውን የወንጀል ድርጊት ሰለመፈጸም አለመፈጸማቸው በፍርድ ቤቱ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት "የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም " በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸው ምስክሮች ቃል እንዲሰማለት በጠየቀው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት የምስክር ቃል ለመስማት ለሁለት ቀን ማለትም ለሕዳር 18 እና ለሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
@Ethionews433 @Ethionews433