የግድያ ፣ የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
ለራሳቸው የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት ለ ሁለት አመታት የግድያ የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ለራሳቸው ስያሜ በመስጠት ለሁለት አመታት የግድያ ፣የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ሰዎች በእስራት እንዲቀጡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ውሳኔ የሠጠ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገልፆል።
እንደ ምስራቅ ወለጋ ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት መግለጫ 11ዱ ግለሰቦች ከ 2014 ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር በተለይ በዋዩ ጡቃ፣ ሌቃ ዱለቻዝ ኩቱ ጊዳ በተባሉ ወረዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የግድያ ፣ የዘረፋ እና የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበረ ሙሉ በሙሉ በማስረጃ መረጋገጡን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።እነዚህ ግለሰቦች በሁለት ምድብ ተከፋፍለው የወንጀል ድርጊቱን ሲፈፅሙ እንደነበረ በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ተጠቅሷል።
የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች ቤቶች በምሽት በማስከፈት በርካታ ገንዘብ እና የሞባይል ስልኮችን ዘርፈው እንደወሰዱ የተጠቀሰ ሲሆን በተጨማሪም የግድያ ወንጀል መፈፀማቸውን በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ተመዝግቧል። ግለሰቦቹ በምስራቅ ወለጋ የተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ የሚፈፅሙትን ወንጀል ድርጊት በመከታተል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልፆል። 11ዱ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የምርመራ መዝገባቸው በፖሊስ ተጣርቶ ለአቃቤ ህግ ተልኳል።
አቃቤ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የክስ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የነፍስ ግድያ እና የውንብድና ተግባር ክስ መስርቷል። በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ለአመታት ሲከታተል የቆየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በነቀምቴ ከተማ ባስቻለው ችሎት በሶስት ግለሰቦች ላይ የ 25 ዓመት እስራት፣ በ ሁለት ተከሳሾች ላይ የ11 አመት ከ ስድስት ወር እስራት ተወስኗል። በሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ ደግሞ ከ ሁለት አመት ከ ስድስት ወር እስከ አንድ አመት እስራት የተወሰነባቸው መሆኑን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ይህኛው መረጃ ያሳያል።
በሰመሃር አለባቸው
@Ethionews433 @Ethionews433