በሦስት ወራት ውስጥ በተከሰቱ 127 አደጋዎች 93 ነጥብ 6 ሚልዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ
👉በአደጋዎቹ የ22 ሰዎች ሕይወት አልፏል
በ2017 ዓ.ም. ብቻ ባጋጠሙ 127 አደጋዎች 93 ነጥብ 6 ሚልዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን እና የ22 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ከደረሱት አደጋዎች 117ቱ በአዲስ አበባ ቀሪዎቹ 10 አደጋዎች ደግሞ በሸገር ከተማ ያገጠሙ ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለአሐዱ በሰጡት መረጃ እንዳሉት፤ ካጋጠሙት አደጋዎች መካከል 63ቱ የእሳት ቃጠሎ፣ 28ቱ የጎርፍ፣ 18ቱ የንግድ ቤቶች ቃጠሎዎች ሲሆኑ 64ቱ ደግሞ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ናቸው፡፡
በደረሱት አደጋዎች ምክንያት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ጨምሮ 12 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
የደረሱትን አደጋዎች ለመቆጣጣር በተደረገ ርብርብ በአደጋ ውስጥ የነበሩ 72 ሰዎችን እና 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉንም የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡
አሁን ያለው ደረቅና ነፋሻማ አየር ድንገተኛ የእሳት አደጋን በማባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚያበረክት ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
(አሐዱ ሬዲዮ)
@Ethionews433 @Ethionews433