ጆ ባይደን ከምርጫው ራሴን ባላገል ዶናልድ ትራምፕን ማሸነፍ እችል ነበር ሲሉ ተናገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዶናልድ ትራምፕን አሸንፈው በህዳር ወር በድጋሚ ወደ ዋይት ሀውስ መግባት ይችሉ እንደነበር ተናግረዋል። ለየት ባለ ቃለ ምልልስ ከዩኤስኤ ቱዴይ ጋር ቆይታ ያደረጉት ባይደን አክለው ለተጨማሪ አራት ዓመታት በጽናት ሀገሪቱን መምራት ይችሉ እንደሆነ ግን እርግጠኛ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። የ82 አመቱ አዛውንት "እስካሁን በጣም ጥሩ ነኝ" ብለዋል። ግን በ86 ዓመቴ ምን እንደምሆን ማን ያውቃል?" ሲሉ ከሱዛን ፔጅ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ ላይ ገልፀዋል።
ከዩኤስኤ ቱዴይ ጋር ባይደን ባደረጉት ቆይታ “በምርጫ ብቆይ አሸንፋለው የሚል እምነት ነበረኝ፣ ግን ዕድሜዬ በቢሮው ቆይታዬ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል መግለፅ እፈልጋለሁ ብለዋል ። "ትራምፕ በድጋሚ ለመመረጥ ሲወዳደር እርሱን ለማሸነፍ ከሁሉ የተሻለው እድል እንዳለኝ አስቤ ነበር።ነገር ግን በ85 አመቴ ወይም በ86 ዓመቴ ፕሬዝዳንት ለመሆን ፈልጌ አልነበረም ሲሉ ተናግረዋል።
ከዩኤስኤ ቱዴይ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ ባይደን እስካሁን ለህትመት ሚዲያ የሰጡት ብቸኛው ከዋይት ሀውስ የመውጫ ቃለ መጠይቅ ነው።ባይደን የሚዲያ ተደራሽነት በዋይት ሀውስ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲሆን ፕሬዝዳንቱ እ.ኤ.አ. ጁላይ 21 ከምርጫ ፉክክሩ ከወጡ በኋላ እንኳን የዜና ኮንፈረንስ አላደረጉም።
በስምኦን ደረጄ
@Ethionews433 @Ethionews433