የትራምፕ አማካሪ የሆኑት ስቲቭ ባኖን ቱጃሩ ሰው ኤሎን ማስክን የክፋት ምሳሌ በማለት በተመራጩ ፕሬዝዳንት ቡድን ውስጥ ክፍፍል መኖሩን አሳዩ
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ አማካሪ ስቲቭ ባኖን አሜሪካን ታላቅ እናደርጋለን በሚለው እንቅስቃሴ ውስጥ በተፈጠረው ውጥረት ኤሎን ማስክን ከዋይት ሀውስ ውጪ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ። ባኖን ከጣሊያን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የቴስላ እና የስፔስኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማስክ የትራምፕን ገቢ አስተዳደር እንዳይጠቀሙ እና "እንደማንኛውም ሰው" እንዲታዩ ለማድረግ የግል ተልእኮ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ማስክ በእውነቱ ክፉ፣ በጣም መጥፎ ሰው ነው። ይሄንን ሰው ማውረድ የግል ስራዬ ነው። በፊት፣ ገንዘብ ስላስቀደመ፣ እሱን ለመታገሥ ተዘጋጅቼ ነበር ፤ ከዚህ በኋላ ለመታገሥ ግን ዝግጁ አይደለሁም ሲሉ ባኖን ለኮሪየር ዴላ ሴራ ጋዜጣ ተናግረዋል። ባኖን በተጨማሪም አክለው እንደተናገሩት የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ የሆነው መስክ ወደ ትውልድ ቦታው "መመለስ" እንዳለበት ተናግረዋል። ቢሊየነሩ የኤች-1ቢ ቪዛ ፕሮግራምን በመጠቀም ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው የውጭ የቴክኖሎጂ ሰራተኞችን ለመቅጠር በይፋ ከተሟገቱ በኋላ ይህ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል።
ለምንድነው ደቡብ አፍሪካውያን፣ ሊያውም በምድር ላይ ካሉት በጣም ዘረኛ፣ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን በዩናይትድ ስቴትስ ስለሚሆነው ነገር ማንኛውንም ዓይነት አስተያየት እንዲሰጡ የፈቀድነው በማለት ባኖን ተችተዋል። የባኖን ንግግር በሲሊኮን ቫሊ ውስጥ የውጭ ሰራተኞች ሚናን በተመለከተ በትራምፕ ተከታዮች መካከል የተፈጠረው ህዝባዊ አለመግባባት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
በስምኦን ደረጄ
@Ethionews433 @Ethionews433