በህፃናት የሚለምኑ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መዉሰድ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ
ህፃናት ይዘው የሚለምኑ በእርግጠኝነት እናት ስለመሆናቸዉ የማይታወቁ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ መኖራቸው ተገልጿል።በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ልጆቻቸውን ማብላት እና ማጠጣት አቅቷቸው ጎዳና ላይ ይዘው የሚለምኑ ቢኖሩም ህፃናትን ተከራይተው በማምጣት እንደ ገቢ ማስገኛ የሚጠቀሙ በርካታ መሆናቸውን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በዚህ ተግባር የህፃናቱ መብት ከመጣሱም በላይ ደህነንታቸው አደጋ ውስጥ በመግባቱ ከህግ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው ገልፀዋል።ወደ እርምጃ ከመገባቱ በፊት ግን ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ የተለያዩ ትምህርቶች እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።ህፃናት ይዘው የሚለምኑ ግለሰቦች ከልጆቹ ይልቅ ስለሚያገኙት ገንዘብ እና ቀጥሎ በገንዘቡ ስለሚጠቀሙት ነገር ብቻ በማሰባቸው፣ የሚደርስባቸውን ተጠያቂነት አይገነዘቡም ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ለልመና የሚወጡት ህፃናት ካደጉ በኋላ ስራ የመስራት ፍላጎታቸው አናሳ ስለሚሆን በዘላቂነት ህይወታቸው ላይ መጥፎ አሻራ እንደሚያኖር ተነግሯል።ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለጉዳዩ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲሉ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
@Ethionews433 @Ethionews433