የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6ቀን2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።
የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን እስካሁን 499 ሺህ 200 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቆ ነበር፡፡
በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በመደበኛና በግል 750 ሺህ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ከተፈተኑ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች መካከል የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 5 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
@Ethionews433 @Ethionews433