አሜሪካ በአንድ ሳምንት ሦስተኛ የአውሮፕላን አደጋ አጋጠማት
******
እናት ልጇን አሳክማ ስትመለስ ከአራት የአውሮፕላን ሰራተኞች ጋር ነው በአሜሪካ ፊላደልፊያ አቅራቢያ አደጋው የተከሰተው።
በፊላደልፊያ ህክምና የተደረገላት ልጅ እና አስታማሚ እናቷ ወደ መኖሪያቸው ሜክሲኮ በመጓዝ ላይ እያሉ ነበር አርብ ምሽት የሚጓዙባት አውሮፕላን መከስከሷ የተሰማው።
ይህን አደጋ ተከትሎ ቤቶች እና ተሽከርካሪዎች በእሳት መያያዛቸውን የሚያመላክቱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እየወጡ ነው።
የፊላደልፊያ ፖሊስ አደጋው መድረሱን ለሲቢኤስ ኒውስ አረጋግጧል።
የፊዴራል አቪዬሺን አስተዳዳር (ኤፍ ኤ ኤ) ደግሞ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ስድስት ሰዎች እንደነበሩ ይፋ አድርጏል።
ከእነዚህም ውስጥ አራቱ የአውሮፕላኗ ሰራተኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ታካሚ ህጻን እና አስታማሚ እናት መሆናቸው ነው የተገለፀው።
በአውሮፕላኗ ውስጥ ከእናት እና ልጅ ውጭ አብራሪ እና ረዳት አብራሪን ጨምሮ ሁለት የህክምና ባለሞያዎች ሁሉም ዜጎቿ መሆናቸውን የሜክሲኮ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
የተከሰከሰችው "ሊርጀት 55" የህክምና አውሮፕላን ወደ መዳረሻዋ ሜክሲኮ በምታደርገው በረራ ስፕሪንግፊልድ አየር ማረፊያ ነዳጅ ለመሙላት የማረፍ እቅድ እንደነበራት ተገልጿል።
ይሁን እንጂ መነሻ አውሮፕላን ማረፊያውን ከለቀቀች ከ30 ሴኮንድ በኋላ መከስከሷ ነው የተነገረው።
አነስተኛ የህክምና አውሮፕላን መከስከሷን ተከትሎ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ሰሜን ምስራቅ ፊላደልፊያ በማቅናት የነፍስ አድን ስራ ላይ እየተረባረቡ ነው።
አሜሪካ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ሶስት የአውሮፕላን አደጋ አጋጥሟታል።
እስካሁን ስለተሳፋሪዎቹ በህይወት መኖርም ይሁን አለመኖር በግልጽ የተባለ ነገር የለም ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።
ሀብተሚካኤል ክፍሉ
@Ethionews433 @Ethionews433