የትራምፕ ህገወጥ ስደተኞችን የማፈናቀል ፖሊሲ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ችግር መፍጠሩ ተነገረ
ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን በያዙ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ፕሬዝዳንቱ የድንበር ደህንነትን ለመቆጣጠር ባደረጉት ሙከራ ከ8,700 በላይ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ከአሜሪካ ተባርረዋል። የትራምፕን እርምጃ በመቃወም በመላው የአሜሪካ ከተሞች ሰፊ ተቃውሞ ቢደረግም ስደተኞችን ወንጀለኞች በማለት ይፈርጃሉ። አስደንጋጭ በሆነው እርምጃ የትራምፕ አስተዳደር በስደተኞች ጉዳይ ላይ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የነበራቸው 20 የኢሚግሬሽን ዳኞችን ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በማለት በቅርቡ ከስራ አሰናብተዋል።
ይህው እርምጃ ቤተሰቦች እንዲለያዩ እና ህጻናት ያለ ምንም የድጋፍ ስርዓት በማስቀረት ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰነድ አልባ ስደተኞች እጣ ፈንታ በእርግጠኝነት አይታወቅም።የጥገኝነት ጉዳዮች ለመታየት እና ለመጨረስ አመታትን ሊወስድ ይችላል፣ እናም ብዙ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ማስፈጸሚያ ህጋዊ ሂደታቸውን እንዲቆም እና ቤተሰቦቻቸው ሊለያይ ይችላል በሚል ፍራቻ ስራ እና ትምህርት ቤት ለመቅረት እየተገደዱ ይገኛል።
የስደተኞች ጠቀሜታ እና አስተዋፅዖ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሰው ኃይል ውስጥ የማፈናቀል ዘመቻው በኢኮኖሚው ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅእኖ የከፋ እንደሚሆን የኢኮኖሚ ተንታኞች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ዩናይትድ ስቴትስ በስደተኛ እና በተለይም ሰነድ አልባ በሆኑ ዜጎች ጉልበት ላይ የተደገፈች ነች።ስደተኞች የኢኮኖሚው ምሰሶ በመሆናቸው ወደ ስራ መግባት ትተው መደባበቅ መጀመራቸው ችግሩ አፍጥጦ እንደሚታይ ያሳያል ብለዋል።
በስምኦን ደረጄ
@Ethionews433 @Ethionews433