የመከላከያ አቅሞችን የምናጎለብተው “ለመዋጋት አይደለም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
ኢትዮጵያ የመከላከያ አቅሟን የምታገጎለብተው “ትናንሽ አቅም ይዘው ለሚሳሳቱ ኃይሎች ብዙ ጊዜ እንዲያስቡ ለማስቻል” እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እነዚህን አቅሞች የምናጎለብተው ለመዋጋት አይደለም። ውጊያን ለማስቀረት ነው” ብለዋል።
አብይ ይህን ያሉት “ስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ” የተባለ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ማምረቻ ትላንት ቅዳሜ የካቲት 29፤ 2017 በመረቁበት ወቅት በሰጡት ገለጻ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ፤ የትላንቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።
ባለፈው ረቡዕ በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ኢትዮጵያ ከወታደራዊ ግብዓት አንጻር የነበረባትን “ውስንነት ከሞላ ጎደል ፈትታለች” ብለው ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋብሪካ ጉብኝትም ሆነ ያቀረቡት ገለጻ፤ ኢትዮጵያ “ከኤርትራ ጋር ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለመግባት በዝግጅት ላይ ለመሆኗ ማሳያ” አድርገው የቆጠሩ ወገኖች አሉ።
ይህን አመለካከት የተረዱ የሚመስሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትላንቱ ገለጻቸው፤ “እነዚህን አቅሞች የምናጎለብተው ለመዋጋት አይደለም። ውጊያን ለማስቀረት ነው። ትናንሽ አቅም ይዘው ለሚሳሳቱ ኃይሎች፤ ብዙ ጊዜ [ሰጥተው] እንዲያስቡ ለማስቻል ነው። ውጊያን ለማስቀረት (deter) ለማድረግ ከፍተኛ አቅም ስላለው ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@Ethionews433 @Ethionews433