ኢትዮጵያ በሩብ ዓመት ውስጥ ብቻ ከጥይት ሽያጭ 30 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ለውጭ ሀገራት ከሸጠቻቸው ጥይቶች፤ “ከ30 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ” ገቢ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ሀገሪቱ ለውጭ ሀገር ገበያ የሚቀርቡ ክላሽ፣ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ዲሽቃ፣ ታንክ እና ሁሉንም አይነት መድፎች “የማምረት አቅም ያለው” ፋብሪካ መገንባቷንም አብይ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ያሉት፤ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ በቶኬ ኩታዬ ወረዳ የሚገኘውን የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ ትላንት ረቡዕ የካቲት 26፤ 2017 በጎበኙበት ወቅት ነው።
አብይ በዚሁ ወቅት በሰጡት ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ “በተወሰነ ደረጃ” ጥይት እና መሳሪያ “የማምረት ሙከራዎች” እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በ2015 ዓ.ም በአምቦ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ውስጥ ተከላው የተጀመረው ዘመናዊ ፋብሪካ፤ “ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ” ጥይቶችን እና የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎችን ወደ ማምረት መሸጋገሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ይፋ አድርገዋል።
በ2014 ዓ.ም “ጥይት እንገዛ ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ “እነዚህን አይነት ነገሮች ከመግዛት ወጥተን፣ አምርተን፣ ለሌሎች የምንሸጥ ሀገር መሆናችን እና በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄ አቅም ተገንብቶ በማየቴ በጣም ከፍተኛ ክብር እና ደስታ ይሰማኛል” ሲሉ ስሜታቸውን አጋርተዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15258/
@EthiopiaInsiderNews