በትግራይ “ከመንግስት እውቅና ውጪ” የሚደረግ የሰራዊት እንቅስቃሴ “በአስቸኳይ” እንዲቆም አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ
በትግራይ ክልል “ከመንግስት እውቅና ውጪ” የሚደረግ የሰራዊት እንቅስቃሴ “በአስቸኳይ እንዲቆም” የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትዕዛዝ ሰጡ። ይህን ትዕዛዝ ቸል በሚሉ አካላት ላይ “አስቸኳይ” “የእርምት እርምጃ” እንዲወሰድም አሳስበዋል።
አቶ ጌታቸው ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላም እና ጸጥታ ካቤኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ለሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በጻፉት ደብዳቤ ነው።
ከሁለት ቀናት በፊት የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስር በሚተዳደረው “ድምጺ ወያነ” ቴሌቪዥን ጣቢያ በኩል ይፋ የተደረገው በዛሬው ዕለት ነው።
“ህገወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ስለማሳሰብ” በሚል ርዕስ ስር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ “ህገ ወጥ ጉባኤ ያደረገው” በሚል የሚጠራውን ቡድን “ስልጣን ለማግኘት እንቅስቃሴ” እያደረገ እንደሆነ ይወነጅላል።
አቶ ጌታቸው የቡድኑን ማንነት በደብዳቤያቸው በግልጽ ባያስቀምጡም፤ ከዚህ ቀደም ባወጧቸው መግለጫዎች በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራ ስብስብ የህወሓትን “ህገ ወጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጓል” በማለት ሲተቹ ቆይተዋል።
ይህ ቡድን “የሰራዊት አመራሮች ውሳኔ” በሚል ጀምሮታል ያሉትን “ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዲያቆም” የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መወሰኑን አቶ ጌታቸው በደብዳቤያቸው አስታውሰዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15283/
@EthiopiaInsiderNews