ቪዲዮ፦ በአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጥር 29፤ 2017 የተቀሰቀሰው የእሳት አደጋ እስከ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 29 በቁጥጥር ስር አለመዋሉን የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ ቲፎ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ለእሳት ቃጠሎው መከሰት መንስኤ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተይዘው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙት ስድስት ፓርኮች ውስጥ አንዱ የሆነው የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙት የምኒልክ ድኩላ፣ የደጋ አጋዘን፣ ቀይ ቀበሮ እንዲሁም የሌሎች እንስሳት መኖሪያ ነው። በ2003 ዓ.ም በብሔራዊ ደረጃ የተመዘገበው ፓርኩ፤ 84,100 ሄክታር የሚሸፍን ቦታን የሚያካልል ነው።
በፓርኩ የእሳት አደጋ ሲቀሰቀስ በዚህ አመት ብቻ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከጥር 9 እስከ ጥር 22 በቆየ የእሳት ቃጠሎ አደጋ፤ ከ200 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል መቃጠሉን አቶ መሀመድ ገልጸዋል። እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ባልጠፋው የእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰበት የፓርኩ ክፍል ምን ያህል እንደሆነ በወል እንደማይታወቅም አመልክተዋል።
🔴የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የእሳት ቃጠሎው የተነሳበት የጢቾ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የሰጡትን አጭር ቃለ ምልልስ ይህን ሊንክ https://youtu.be/XUqweudgk90 ተጭነው ያድምጡ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@EthiopiaInsiderNews