በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ በተከሰተ የአተት ወረርሽኝ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ጃዊ ወረዳ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት (አተት) ወረርሽኝ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳደር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ። በወረዳው በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40 ገደማ መድረሱን የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የአተት ወረርሽኙ መጀመሪያ የታየው፤ በወረዳው በሚገኘው ብሔራዊ ቀበሌ ፍልውሃ በሚባል ጸበል ቦታ እንደሆነ የጃዊ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንበር ግርማ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች፤ ወደዚህ ጸበል ቦታ ከመምጣታቸው አስቀድሞ በባህርዳር ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አንዳሳ በሚባል ጸበል ቦታ እንደነበሩ መረጋገጡንም አስረድተዋል።
በአተት ወረርሽኝ መያዛቸው በምርመራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተረጋገጠው ሁለት ሰዎች እንደነበሩ የገለጹት የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ከሁለት ቀን በኋላ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 መድረሱን የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊው ገልጸዋል።
“በሁለት ቀን ውስጥ ይሄንን ያህል ኬዝ ገጥሞን አያውቅም። ከዚህ በፊት እንደዚህ አልገጠመንም። በ24 ሰዓት ውስጥ ወደ 20 ሰዎችን ማግኘት ማለት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ አቶ መንበር የሁኔታውን አሳሳቢነት አመልክተዋል።
🔴 ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15630/
@EthiopiaInsiderNews