የኢቢኤስ ቴሌቪዥን እና ሶስት የጣቢያው ሰራተኞች በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተከሰሱ
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ እህት ኩባንያው እና ሶስት የጣቢያው ሰራተኞች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል ክስ ቀረበባቸው። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበው በዚህ የክስ መዝገብ ክስ፤ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ፣ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን “ሀሰተኛ ታሪኳ ተሰራጭቷል” የተባለችው ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች በሽብር ወንጀል ተከስሰዋል።
በአጠቃላይ 16 ተከሳሾች የተካተቱበትን የክስ መዝገብ፤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 28፤ 2017 ያቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ነው። ከተከሳሾቹ መካከል ስምንቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቢሮ እና በወረዳ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ናቸው።
ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው መዝገብ ሶስት የክስ አይነቶች ጠቅሷል። የመጀመሪያው ክስ፤ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በ2011 ዓ.ም. የወጣን አዋጅ በመተላለፍ የቀረበ ነው። ዐቃቤ ህግ በክሱ የጠቀሰው የአዋጁ ድንጋጌ፤ “የሽብር ድርጊት” በመፈጸም “የሰው ህይወትን ለአደጋ ማጋለጥን” ይመለከታል።
ይህ ድንጋጌ ተጠቅሶ ክስ ከቀረበባቸው ተጠርጣሪዎች ውስጥ በቀዳሚነት የተቀመጡት በአሁኑ ወቅት ነዋሪነታቸውን በውጭ ሃገር ያደረጉት ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ተስፋዬ ወልደስላሴ ናቸው።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15811/
@EthiopiaInsiderNews