በሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚታየው የምሁራን ተሳትፎ ከሚጠበቀው አንጻር “አነስተኛ ነው” ተባለ
በኢትዮጵያ ያሉ ምሁራን በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ ያላቸው ተሳትፎ፤ ሊኖራቸው ከሚገባው “አስተዋጽኦ” አንጻር ሲታይ “አነስተኛ ነው” ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ተናገሩ። አብዛኞቹ ምሁራን ከሂደቱ “ራሳቸውን የማግለል” አሊያም ሁኔታውን “በዝምታ የመመልከት” አካሄዶችን የመከተል “አዝማሚያዎች” እንደሚታይባቸውም ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ይህን የገለጹት፤ በሀገራዊ የምክክር ሂደት ምሁራን የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 9፤ 2017 በተካሄደ የውይይት መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። በአዲስ አበባው ሃይሌ ግራንድ ሪዞርት በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ከአማራ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተመረጡ 90 ምሁራን ተሳትፈዋል።
ይህን መርሃ ግብር በንግግር የከፈቱት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ፤ በሌሎች ሀገራት የተከናወኑ ሀገራዊ ምክክሮች “ውጤታማ እንዲሆኑ” ካደረጓቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ “የምሁራኖቻቸው አስተዋጽኦ” እንደሆነ አስገንዝበዋል። ምሁራን ሀገራዊ ምክክርን “በተለየ መልኩ ማየት አለባቸው” የሚል አቋም ኮሚሽኑ እንዳለው የጠቀሱት ሂሩት፤ ጉዳዩ “በአመለካከት ልዩነቶች ሳይጋረዱ” “ያለስስት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱለት የሚገባ” እንደሆነም አሳስበዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15933/
@EthiopiaInsiderNews