የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያንን የመቅጠር እቅድ እንዳላት ገለጸች
ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) እንደገለጸው ከሆነ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊን ይኖራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ አረብ ኢምሬት ከተሞች እየሄዱ እና እየተቀጠሩ ይገኛሉ፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ በቀጣይ ከቤት ሰራተኞች በተጨማሪ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊንን የመቅጠር እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሚኒስትር ሱልጣን አል ሻምሲ በአዲስ አበባ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ሚንስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ እንዳሉት “በዩኤኢ ከተሞች ብዙ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ በቀጣይ በቱሪዝም፣ ሆቴል፣ ቴክኖሎጂ እና ንግድ ሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊንን የመቅጠር እቅድ አለን” ብለዋል፡፡
@Ethiopian_Digital_Library