በ2017 የትምህርት ዘመን ከ50ሺ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል
በአዲስ አበባ በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች የ2017 ዓመት 50ሺ 807 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ኦን ላይን በውጤታማነት ለመስጠት በሚያስችል ስራ እየተሰራም መሆኑን የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ በውጤታማነት ለመስጠት እንዲቻል ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ለማከናወን እቅድ መዘጋጀቱንና ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል። ፈተናው ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ኮምፒውተሮችና እና መሟላት የሚገባቸውን መሰል ግብዓቶች የመለየት ስራ ተጀምሯል።
ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የማዘጋጀት ተግባራት ከወዲሁ በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሃ ግብር እንዲሰጥ በትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል።
@Ethiopian_Digital_Library