የመምህራን የሥራ ማቆም አድማ
በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከረቡዕ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ መምህራንና የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል፡፡
መምህራኑ፣ ለሥራ ማቆም አድማው መነሻ የኾነው፣ “ጥያቄዎቻችን ምላሽ አለማግኘታቸውና ጥቅማችንን የሚጎዳ አሠራር መጀመሩ ነው፤” ብለዋል፡፡
ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አስተያየት ሰጪዎቹ፣ አድማው ከአንደኛ እስከ ኹለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ድረስ ባሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ እንዲቋረጥና እንዲስተጓጎል ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
#VOA
@Ethiopian_Digital_Library