የካቲት 23 ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረገወ ተዐምር ይኽ ነው፡፡
በዚያን ወራት የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክም ሀገሬ
ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ኹሉ ፈጥኖ ይነሣ፡፡የጦር መሣሪያውን
ተሸክሞ ይከተለኝ ዘንድ በሰመ ማርያም አደራ እላላለሁ ሲል ዐዋጅ አሰነገረ፡፡
ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ በጋሻቸው
እምብርት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ መስቀል
ጠላትን ድር አድራጊ እንደኾነ አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡
ወደ አንዷ የትግራይ አውራጃም ምድረ ዐደዋ ደረሰ፡፡ የዚኽ ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክ ሚስት እቴጌ ጣይቱ(ወለተ ሚካኤል)በንጉሡ ትእዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስ አስይዞ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ማቴዎስና ከቀሳውስቱና መነኮሳቱ ከንጉሡ ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክም ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡ በዚህም ጊዜ ኹላቸው ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ምኒልኮ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ፡፡
ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ይኸውም ወርኃ የካቲት ኻያ ኹለትቀን ነው፡፡ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ዓፄ ምኒልክም የጦር ልብሱን ለብሶ ከሠራዊቱ ጋር ጦር ግንባር ገባ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ 11ሰዓት ጦርነቱ
ተጀመረ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ቅዶስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመሔድ እጅግ በሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይል ቃል በጦርነቱ መኻል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር፡፡
በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ዓፄ ምኒልክ በጦርነቱ መኻል ሳለ ሊቀ
ጳጳሳቱ አባ ማቴዎስና ኹላቸው ካህናትም ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኃላ ቆመው ጸሎተ ምሕላ ያደርሱ ነበር፡፡
ንግሥቲቱ እቴጌ ጣይቱም በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ
አትለይም ነበር፡፡ ኹላቸው ካህናትም በአምላካቸው እግዚአብሐር የሕግ ታቦት
ፊት መለከት ይነፋ ነበር፡፡
በዚህም ዕለት ይኸውም በወርኃ የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና
በኢትዮጵያውያን መካከል ከፈተኛ ጦርነት ኾነ፡፡ በሰማይም ታላቅ ተዐምር
ተደረገ፡፡ የቀስተ ደመና ምልክት ታየ፡፡ ከቀስተ ደመና ውስጥ መልኩ አረንጓዴ
የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር እንደ ክረምት ነጎድጎድ ያለ ድምፅም ተሰማ፡፡
ከዚኽ የነጎድጎድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና
ሽብር ሆነ ለመዋጋትም አልቻሉም፡፡
ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተዐምር ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነፋስ ይልቆ እየሀፋጠነ በዓየር ላይ በተገለጸ ጊዜ ሮማውያን በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ፡፡ እንግዲህ ማን ያድነናል አሉ፡፡ ምድር ጠበበቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን ጦር ሠራዊት ፈጇቸው፡፡
የተረፋትንም ማረኳቸው ፈጽመው እስኪያጠፏቸውም በሮማውያን ላይ
የእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያን እጅ እየበረታች ሔደች፡፡
የኢትያጵያው ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ
በእግዚአብሔር ኃይል በገባሬ ተዐምራት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት
የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርጎ የድል አክሊል ተቀዳጀ፡፡
በነቢዩ ዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔር ባለ ዘመኔ ኹሉ አመሰግነዋለሁ ለፈጣሪዬ እዘምራለሁ አለ፡፡
ሕዝቡም ኹሉ በክብር ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና
እናመሰግነዋለን የሮማዉያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም
ሰባብሯልና ሠራዊቱንም ኹሉ በምድር ላይ በትኗልና እያሉ አመሰገኑ፡፡
በፈጣሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መኻል የረዳቸው ቅዱስ
ጊዮርጊስንም በፍጹም አደነቁ፡፡ የሮማ የጦር ሠራዊትም በኢትዮጵያውያን ፊተቀ ተዋረዱ ዳግኛም በኢትያጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም፡፡
ይኽ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክም ከዐድዋ ጦርነት
ከተመለሰ በኃላ የኹላቸው ኢትዮጵያውያን ከተማቸው በኾነች ዋና ከተማ አዲስ
አበባ መኻል በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ሕንፃ ክርስቲያን ተከለ፡፡
ስሟንም ገነተ ጽጌ ብሎ ሰየማት፡፡
ንጉሡ ሚኒሊክን ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታና ሀገሩ
ችግር በገጠማት ጊዜ ኹሉ ይረዳው ነበር፡፡
የኃያሉ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎቱና በረከቱ ከኹላችን
ኢትያጵያውን ጋር ይኹን፡፡
ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያንም በነፃነት ይጠብቅልን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ)
https://t.me/Ethiopian_Ortodoks