የነዳጅ ማስተካከያ ባለመደረጉ ምክንያት በ 2 ወራት ዉስጥ ብቻ ከ 30 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ሊመጣ እንደቻለ ተገለፀ
የነዳጅ ግብይትን እና የነዳጅ ማደያዎችን ተደራሽነት ህጋዊነት ለማረጋገጥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የነዳጅ እና ኢነርጅ ባለስልጣን ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተነግሯል።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደተናገሩት " የጎረቤት ሀገራትን በነዳጅ ለመቀለብ የተዘጋጁ ማደያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ በሁለት ወራት ብቻ የነዳጅ ማስተካከያ ባለመደረጉ 35 ቢሊዮን ብር እዳ ሊመጣ እንደቻለ" አስረድተዋል።
ይህ የተገለፀዉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከአስረጂዎች ጋር በተወያየበት ወቅት ነዉ።
ሚኒስትሩ እንዳሉት አሁናዊ የነዳጅ አቅርቦት ፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ ብክነት ስላለ ይህ ችግር ለመፍታት ረቂቁ የማይተካ ሚና እንዳለው በአፅንኦት ተናግረዋል ።
የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል በሚል እሳቤ ነዳጅ እያለ ነዳጅ የለም ብለው የሚዘጉ ማደያዎች መኖራቸውን የጠቀሰው ሚኒስትሩ ረቂቁ በአስመጭዎች፣ አከፋፋይ እና ማደያዎች ላይ ህጋዊ ስርዓት ለመዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily