ትምህርት ሚኒስትር " የመምህራን ባንክ" ለማቋቋም ሀሳብ እንዳለዉ አስታወቀ
ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን የገለፀው ትምህርት ሚኒስትር
መምህራን "በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስችል የመምህራን ባንክ" የማቋቋም ሀሳብ እንዳለዉ ፍንጭ ሰጥቷል።
ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ( ፕ/ር) እንደተናገሩት ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆኑ ይህንን ለማስተካከል " ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ስርዓቶች ይዘረጋሉ" ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባም አስረድተዋል ።
ይህ የተባለዉ የትምህርት ሚኒስቴርን የበጀት ዓመቱ የ3 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ በሚመለከት ከሚመለከተዉ አካል ጋር ዉይይት ባደረገበት ወቀት ነዉ።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily