የዉጪ ምንዛሪ ለዉጡን ተከትሎ ከግምት ዉስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ
መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ተረድታለች።
የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።
አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ዉስጥ 122 በመቶ ደርሷል።
ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ አለም ባንክና የአለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ አለምአቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሬ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸው ነዉ ለማወቅ የተቻለው።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily