ቦይንግ ከአቀደው ከስድስት ወራት በኋላ የአፍሪካ ዋና ቢሮዉን በአዲስ አበባ ከፈተ
የአሜሪካው ግዙፍ የኤሮስፔስ ኩባንያ ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽ/ቤቱን በአዲስ አበባ ዛሬ ከፈተ። ኩባንያው ቀደም ሲል ይህንን ቢሮዉን በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ለመክፈት እቅድ የያዘ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቶ ነበር። ይሁን እንጂ ከስድስት ወራት መዘግየት በኋላ ዛሬ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የኩባንያው አመራሮች ተገኝተዋል። ሚኒስትሩ ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ አቪዬሽን ውስጥ የኢትዮጵያን ሚና እንደሚያሳድግና ለአህጉሪቱ እድገት ወሳኝ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ከአስራ አንድ ወራት በፊት የአሜሪካው ግዙፍ ኩባንያ ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ቢሮዉን በኢትዮጵያ ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ። ይህ ውሳኔ ኬንያ ወይም ደቡብ አፍሪካ ለዚህ መስፋፋት ተመራጭ ቦታዎች ይሆናሉ የሚለውን ግምት ያቆመ ነበር።
ቦይንግ በ2023 ከኢትዮጵያ ጋር የነበረውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በኢትዮጵያ የተወሰኑ የአውሮፕላን ክፍሎችን በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily