25ኛ ዓመት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ህዳር 14 / 2018 ዓ.ም. ይካሔዳል
የብር ኢዮቤልዩ ላይ የደረሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሊከናወን ሰባት ወራት ቀሩት። ህዳር 16 ቀን 1994ዓ.ም. ጅማሮውን ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በቀጣይ ህዳር 14 ቀን 2018ዓ.ም. 25ኛ ዙር ውድድሩን ያከናውናል።
ከአፍሪካ ትልቁ የ10ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር የሆነው ዝግጅቱ ባለፉት 24 የውድድር ዓመታት ወደ 760ሺህ አካባቢ ሰው በ10ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ አሳትፏል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዘንድሮ ውድድር በተጠናቀቀ ማግስት የ25ኛ ዓመት ክብረበዓሉን አስመልክቶ ለቀጣዩ ዓመት 500 ቀዳሚ ተሳታፊዎች በነጻ ምዝገባ ያከናወነ መሆኑ ይታወሳል። ለሌሎች የውድድሩ ተሳታፊዎች ምዝገባ ሐምሌ ወር ላይ እንደሚከናወን ተገልጿል።
“25ኛ ዓመታችንን አብረውን በመሆን ካበረቱን ሁሉ ጋር ለማክበር ተዘጋጅተናል ፤ ደስታችንን ከራሳችን ለመጀመር በዚህ እሁድ ኬንያ በሚደረገው ኤልዶሬት ማራቶን ላይ ተሳትፈን እና ሩጫችንን አስተዋውቀን እንመለሳለን።” ያሉት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “ከወዲሁ ከሩጫችን ጋር የተያያዙ የተሳታፊዎቻችንን ልዩ ልዩ ታሪኮች እና ገጠመኞች መሰብሰብ ስለጀመርን በማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችን ላይ ቢነገር የሚሉትን ትውስታቸውን ያካፍሉን” ሲሉ ለተሳታፊዎች ጥሪ አቅርበዋል።
ከ24 ዓመታት በፊት ውድድሩ ሲጀመር ኃይሌ ገብረስላሴ እና ብርሃኔ አደሬ የመጀመሪያውን ዓመት ውድድር ያሸነፉ አትሌቶች ሲሆኑ ፤ በዘንድሮ ውድድር ላይ ወጣቶቹ አትሌቶች ቢንያም መሃሪ እና አሳየች አይቸው ማሸነፋቸው ይታወሳል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily