በአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ 5ኛ ዙር ጨረታ ከፍተኛው ዋጋ በካሬ 265 ሺህ ብር ተመዘገበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባካሄደው 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።
በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች ለ427 ፕሎቶች ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር ከፍተኛው ዋጋ 265 ሺህ ብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተመዝግቧል።
የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በዚህ ዙር ጨረታ ከፍተኛ ተወዳዳሪነት የታየ ሲሆን፣ በተለይም ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ተሰጥቷቸዋል
ይህ ውጤት ከዚህ ቀደም ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአስር ክፍለ ከተሞች በተካሄደው በ4ተኛዉ ዙር የሊዝ ጨረታ ከነበረው ከፍተኛ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው። በወቅቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አንድ ካሬ ሜትር መሬት በ306 ሺህ 600 ብር ከፍተኛ ዋጋ ተመዝግቦ እንደነበር ካፒታል መዘገብ ይታወሳል። በንፅፅሩ ዝቅተኛው ዋጋ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 12 ሺህ 320 ብር ነበር።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily