በኢትዮጵያ ለ7 ጊዜ የሲቪል ምዝገባ ቀን በሀዋሳ ከተማ ተከበረ።
ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ የሲቪል ምዝገባ ቀን በዓልን "በዲጂታላይዜሽን የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስን ከህጋዊ መታወቂያ ሥርዓቶች ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር አካታችነትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
የሲቪል ምዝገባ ስርዓት ዋነኛ ተግባር መረጃ ማመንጨት ነው፡፡ በአንድ አገር ዜጎች ላይ ከልደት እስከ ህልፈተ ህይወት የሚከሰቱ ክስተቶችን በቀጣይነት ፣በቋሚነትና በአስገዳጅነት በመመዝገብና በማከማቸት በዋነኛነት ለህግ፣ለአስተዳደርና ለስታትስቲክስ ፍጆታ ይውላሉ፡፡ በምዝገባው ስርዓት የሚመዘገቡና የሚሰበሰቡት መረጃዎች በግለሰቦች፣ በማህበረሰብ እና በመንግስት ደረጃ በቅንጅት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው፡፡ መንግስት የሲቪል ምዝገባ አስፈላጊነት በመገንዘብ በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት እና ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች እና አለም አቀፋዊ የሲቪል ምዝገባ መርሆችን በጠበቀ መልኩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስር በሚገኙ በገጠርና በከተማ ቀበሌዎች የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ ፣ የሞት እና የጉዲፍቻ ኩነቶች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታትስቲክስ በአፍሪካ ትልቅ ትኩረት በማግኘት በአፍሪካ ሕብረት አባል አገራት በነሐሴ ወር እንዲከበር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በሰፊው እንዲሰራ በተወሰነው መሰረት በአህጉርና አገር አቀፍ ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ በነሐሴ ወር ተከብሯል፡፡ የሲቪል ምዝገባ ቀን ማክበር ያስፈለገበት ዓላማ ምዝገባው ዘርፈ- ብዙ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ የምዝገባው ስርዓት በአስተማማኝ መልኩ ተግባራዊ አንዲሆን ሁሉም የሚመለከተው አካል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ እና ህብረተሰቡ ኩነቶችን ማስመዝገብ ያለውን ጠቀሜታ በማስገንዘብ ረገድ ያለው ተሳትፎ እንዲጎለብት ማነቃቃት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
በሲቪል ምዝገባ ቀን ላይ ተገኝተው መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተከበሩ ወ/ሮ ፍንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ እንዳሉት “በአገራችን የሲቪል ምዝገባ ስርዓትን መዘርጋት ያስፈለገበት መሰረታዊ ጉዳይ ዜጎች ሕገ-መግስታዊ መብታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኙ ለማድረግ ፣በየጊዜው የሚወጡ ሕጎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በተሟላ መረጃ እንዲደገፉ ለማስቻል እንዲሁም በተገቢው ሥራ ላይ መዋላቸውን ለማረጋገጥ ከምዝገባ ሥርዓቱ የሚመነጩ መረጃዎች የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡” ክብርት አፈ-ጉባኤ በመክፈቻ ንግግራቸው “በአገራችን የሲቪል ምዝገባ ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ የፍትህ አካላት ዘመናዊና ቀልጣፋ የመረጃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲኖራቸው እና የህዝብ አስተዳደር ስርዓትን ለማስፈን ትክክለኛ እና ፍትሃዊ ውሳኔዎችን ለመስጠት አስፈላጊ ነው ያሉት የኘሬዘዳንቱ አማካሪ ዜጎች ለሚያነሷቸው የማንነት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከልማዳዊ አሰራሮች ወጥተው ህጋዊና አስተማማኝ የመረጃ ስርዓት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለአንድ አገር ቀጣይ እድገት አቅጣጫን ለመንደፍ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:- https://www.facebook.com/ICSEthiopia/posts/pfbid0hyB5Bm3dd1jZgUL5ACjuRtB1g467oh9zGucFSKE7Pzrcab4hxap8F7FM1r4YWjbAl
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/