28ተኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች የጋራ ስብሰባ ተጀመረ
________________________
(ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።
28ተኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች የጋራ ስብሰባ ልዑክ መሪ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢትዮ-ጅቡቲ ግንኙነት ከጋራ ድንበር አስተዳደር ባለፈ አገራቱ ያላቸው የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ እና ደህንነትን በማስከበር የጋራ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አውስተዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢጋድ በማዕቀፍ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ጉልህ መሆኑን ጠቁመው ፤ ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች በኤሌክትሪክ ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና በንግድ እረጅም ዘመን ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኘነት እንዳላቸው ተናግረዋል ።
የጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ጸሃፊ ሱሉማን ሙአሚን በበኩላቸው የኢትዮ ጅቡቲን መልካም ግንኙነት ወደፊት ለማስቀጠል በጋራ እንደሚሰራ በመግለፅ በድንበር ጉዳዮች ላይ በተለይም የጋራ መሰረተ ልማትን በትብብር በማጠናከር የጋራ ራዕያችንን እንደምናሳካ አልጠራጠርም ብለዋል፡፡
ዋና ጸሃፊው የሀገራቱ ግብ እና ራዕይ ተመሳሳይ በመሆኑ በሰላም እና ደህንነት በጋራ በመሆን ልማታችንን በማሳደግ ተጠቃሚነታችንን እናረጋግጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊ ት በሀገራቱ ድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ፣የሽብር እንቅስቃሴዎች እና ህገ ወጥ ንግድን በጋራ በመከላከል እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ጥቅም እንዲጠበቅ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ለሁለት ቀናት ቆይታ የሚያደርገው ስብሰባ የድንበር አስተዳደር፣ የንግድ ግንኙነት እና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ላይ ትኩረቱን በማድረግ ውይይቱ ይካሄዳል ።
በስብሰባው የሁለቱ አገራት የኢሚግሬሽን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የንግድ የፀጥታ እና ደህንነት ፖሊስ፣ የመከላከያ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/