28ኛው የኢትዮጵያና ጂቡቲ የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎችና ኮሚሽነሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ።
ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም
የ28ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የድንበር አስተዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች ልዑክ መሪ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፥ ይህንን ስብሰባ ለ28ኛ ዙር ማከናወናችን የጀመርነውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ማሳያ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ያለንን ፍላጎት ይመሰክራል ብለዋል።
አክለውም ያደረግናቸው ግልጽ ውይይቶች ያሉብንን የጋራ ተግዳሮቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በግልጽ ማሳያዎች ሲሆኑ ከዚሁ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ትብብር ያጠናክረዋል ብለዋል።
በሁለት ቀን ቆይታቸው የ27ኛው ዙር ጉባኤ አፈጻጸሞች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም በቁልፍ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንና የጋራ ድንበሮችን በተሻለ መንገድ ለማስተዳደር፣ በድንበር አካባቢ ያለውን ሰላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ እና የጋራ የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል በሚደረገው የጋራ ጥረት አተገባበር ላይ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል።
እንዲሁም የህዝቦችን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ እና ለማበረታታት የትብብር ዘዴዎችን በመቀየስ የኮንትሮባንድ ተግባራትን፣ የጦር መሳሪያ ዝውውርን፣ ሕገወጥ የሰዎች ፍልሰትን፣ የኮንትሮባንድ እና ሌሎች አገር አቀፍ ወንጀሎችን ጨምሮ የተለመዱ ተግዳሮቶችን መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት ውይይት የተደረገባቸው አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ እና ግምገማ እንዲሁም ለተግባራዊነታቸው ቁርጠኝነት የሚጠይቁ ሲሆን ለዚህም በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም በስብሰባው ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/