ዓሹራን ለመውሊድ?
~~~~~~
የዓሹራን ፆም ለመውሊድ መረጃ አድርጎ ማቅረብ ከሱፍዮች ዘንድ የተለመደ ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው፦ ነብዩ ﷺ ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶች ዓሹራን ሲፆሙ አግኝተዋቸው ነበር። የሚፆሙበትን ምክንያት ሲጠይቋቸው “አላህ ፊርዐውንን አስጥሞ ሙሳን ያተረፈበት ቀን ስለሆነ ነው” ይላሉ። በዚህን ጊዜ ነብዩ ﷺ “ለሙሳ እኛ ከናንተ ይበልጥ የተገባን ነን” አሉ። እናም ይህንን መነሻ በማድረግ ለሙስሊሞች ትልቅ ድል የተገኘባቸውን እለቶች አስቦ መዋል እንደሚቻል ሐዲሡ ያመላክታል ይላሉ።
ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ፡-
1. እና ለምን ገናን ከክርስቲያኖች ጋር አታከብሩም? ዒሳ የኛ ነብይ አይደሉም የሚል አንድ ሱፊ ሰምቻለሁ። እንግዲያው ሙሳም የናንተ ነብይ አይደሉምና ታሪካቸውን አታጣቅሱ። ዓሹራንም አትፁሙ። ሂሳባችሁ ይህንን ነው የሚሰጠው።
2. የዓሹራ ፆም ማስረጃ የሚሆናችሁ ከሆነ ለምን ዓሹራንም በጭፈራ አታከብሩትም? ለምን ዓሹራው ላይ ያለው ፆም አልበቃችሁም?
3. ስለዚህ ዓሹራእና መውሊድ አፈፃፀማቸውም ለየቅል ነው። ሱናው ፆም ሲሆን ቢድዐው ግን መብላት፣ መጨፈር ነው። እናም ማስረጃው ያስኬዳል ቢባል እንኳ እለቱን መፆም ላይ የሚገደብ ነበር። ይህንን ነጥብ ለመዝለል የመውሊድ አክባሪዎች የሚሰሩት ውሽልሽል ምክንያት እራሳቸውን ከመሸወድ ያለፈ ዋጋ የለውም።
4. ዓሹራን ነብዩ ﷺ እንዲፆም ማዘዛቸው አስተማማኝ መረጃ የመጣበት ሲሆን አመታዊ ልደታቸውን ግን እንኳን በጭፈራ በፆምም አላሳለፉትም። አላዘዙበትምም። ቅንጣት ታክል መረጃም የለውም። ሶሐቦቹም፣ ታቢዒዮቹም፣ አትባዑ ታቢዒንም፣ አራቱ ኣኢማዎችም አላከበሩትም። ይህም የዓሹራእ ጉዳይ ፈፅሞ ለመውሊድ ማስረጃ እንደማይሆን ይጠቁመናል። ስለሆነም ዓሹራእ እራሱን የቻለ ዒባዳ እንጂ የሌሎች ቢድዐዎች መነሻ አይደለም። ያለበለዚያ ለ600 አመታት የሙስሊም ምሁራን ሐዲሡን አልተረዱትም ማለት ነው። ይሄ ከባድ ውንጀላ ነው።
5. በነብዩም ﷺ ይሁን በሶሐቦቹ ዘመን ታላላቅ የአላህ ፀጋዎች የተፈፀሙባቸው ቀናት ብዙ ሆነው ሳለ በየአመቱ ያስቧቸው እንደነበር የሚጠቁም መረጃ አንድም የለም። ለምሳሌ በዚያ ድንቅ ዘመን ከተፈፀሙ እጅግ ትልልቅ የአላህ ፀጋዎች ውስጥ በሒራእ ዋሻ ሳሉ መልአኩ ጂብሪል የሳቸውን ነብይነት ይዞ የመጣበትና የመጀመሪያው ቁርኣን (ኢቅራእ) የወረደበት ቀን፣ በአንድ ሌሊት ከመካ በይተል መቅዲስ ድረስ ተጉዘው፣ ሰማየ ሰማያት ወጥተው ከጌታቸው ጋር ተገናኝተው አምስት ወቅት ሶላቶችን የተቀበሉበት (የኢስራእና ሚዕራጅ) ቀን፣ ነብዩ ﷺ ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱበት ቀን፣ ሙሽሪኮችን በድል ያንበረከኩበት የበድር ዘመቻ ቀን፣ የአሕዛብ ድል፣ አስራ ሶስት አመት ተሰቃይተው በከሃዲዎች ግፍ ምክንያት ጥለዋት የሄዷትን መካን ተመልሰው በድል የተቆጣጠሩባት ቀን፣ ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው። እስኪ ከነዚህ ውስጥ ነብዩ ﷺ የትኛውን ነው በያመቱ ሲያከብሩ የነበረው? በአቡበክር ጊዜም የአፈንጋጮች አከርካሪ የተሰበረበት ጦርነት ተካሂዷል። በዑመር ጊዜም ሙስሊሞች በርካታ ተከታታይ ድሎችን በመጎናፀፍ የዘመኑን ልእለ-ሃያላን አፈራርሰዋል። ለምሳሌ የቃዲሲያ ድል፣ የኒሃውንድ ድል፣ የፈለስጢን፣ የዒራቅ፣ የግብፅ … መከፈት። በዑሥማን ጊዜም በድል ላይ ድል እየደራረቡ ግዛታቸውን አስፍተው እስከ አውሮፓ ዘልቀዋል። በዐሊይ ጊዜም ዐሊይን በደስታ ሱጁድ ያስወረደ ድል በኸዋሪጆች ላይ ተመዝግቧል። በ 41ኛው ሂጅራም ነብዩ ﷺ “ይሄ ልጄ ታላቅ ነው። ምናልባትም አላህ በሱ ሳቢያ ሁለት ትልልቅ የሙስሊም ጎራዎች ያስታርቃል” ያሉት ትንቢት ሐሰን ብኑ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ስልጣናቸውን ለሙዓውያ በማስረከባቸው ምክንያት ለሁለት ጎራ ተከፍለው የነበሩት ሙስሊሞች ህብረትን አጣጥመዋል። [ቡኻሪ፡ 2704] አመቱንም “የአንድነት አመት” በማለት ሙስሊሞች ደስታቸውን ለታሪክ አስተላልፈዋል። እነዚህ ሁሉ አንፀባራቂ ገድሎች ቢመዘገቡም ባለ ገድሎቹ ሶሐቦች ግን በያመቱ እነዚህን ገድሎች እየተሰባሰቡ አይዘክሩም ነበር። ሐዲሡ ስላልገባቸው ነው? ታቢዒዮቹስ? አትባዑት ታቢዒንስ? አራቱ አኢማዎችስ? እነ ቡኻሪ እነ ሙስሊምስ?
6. ሶሐቦችን እንዲህ አይነቱ የመረጃ አጠቃቀም እንዴት ተሰወራቸው? ዘግይቶ የመጣው ትውልድ ከነሱ የበለጠ አላህን አመስጋኝ ነውን? የነብዩ ﷺ ምስጢረኛ የነበረው ሶሐባው ሑዘይፋህ ብኑል የማን ረዲየላሁ ዐንሁ “የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦችና ቤተሰቦቻቸው አላህን ያላመለኩበትን እያንዳንዱን አምልኮት አላህን አታምልኩበት። የመጀመሪያዎቹ ለኋለኞቹ የተውት ቦታ የለምና” ይላሉ። [አዙህድ፡ 47]
7. ደግሞም ሐዲሡ ውስጥ ትልልቅ ፀጋዎች የተገኙባቸውን ቀናት ለማሰብ መረጃ ማድረግ እንደሚቻል ብንግባባ እንኳን ለመውሊድ መረጃ መሆን አይችልም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ከውዝግብ በፀዳ መልኩ አይታወቅምና። በየትኛውም የአመቱ ጊዜ መውሊድን ማክበር ይቻላል የሚሉ ሰዎች ይህንን ሐዲስ ማስረጃ ማድረግ አይችሉም። ምክንያቱም በሐዲሡ ውስጥ ዓሹራእ የሚፆመው ፊርዐውን በሰመጠበት፣ ሙሳን አላህ ባተረፈበት ቀን እንጂ አመቱን ሙሉ ወይም ባሰኛቸው ቀን አይደለምና።
8. በዚያ ላይ ዓሹራእ ለሙስሊሞች ዒድ አይደለም። እንደ ዒድ ከሚያስቡት የሁዶች ለመለየትም ነው ተፁሞ የሚዋልበት አንዱ ምክንያት። ነብዩ ﷺ ይህንን ሐቅ እንዳስተማሩ ተዘግቧል። [ቡኻሪ፡ 2005፣ ሙስሊም፡ 2716፣ 2717] ልብ በሉ! ሙስሊሞች ዘንድ እንኳን እንደ ዒድ ሊታሰብ እንደ ዒድ ከሚቆጥሩት ጋር መመሳሰልም እንዳይኖር “በቀጣይ ከኖርኩ ዘጠነኛውንም እፆማለሁ” ብለው ነበር ነብዩ ﷺ። [ሙስሊም፡ 2723፣ 2723] ስለዚህ ዓሹራን መነሻ አድርጎ ነብዩ ﷺ ከደነገጉት ውጭ ተጨማሪ ዒድ መደንገግ ያፈነገጠ ቂያስ ነው።
~~~~
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor