“በተውሒድ ላይ ያዘጋጀው ኪታቡ ትልቅ ጥራዝ ነው። እሱ እራሱ የአላህን 'ሱራ' በተመለከተ የመጣውን ሐዲሥ በርግጥም ከቀጥተኛ መልእክቱ አዙሯል (ተእዊል አድርጓል)። እንግዲያው አንዳንድ የአላህ መገለጫዎችን ተእዊል ያደረጉ ሰዎችንም ዑዝር ይስጥ። ቀደምቶች በተእዊል ውስጥ አልገቡም። ይልቁንም በቀጥታ አምነዋል። ከተእዊልም ተቆጥበዋል። የዚህን እውቀት (ሐቂቃውን) ወደ አላህና መልእክተኛው አስጠግተዋል። ኢማኑ ትክክለኛ፣ ሐቅን ለመከተል የሚያልም የሆነን ሁሉ በኢጅቲሃዱ በተሳሳተ ቁጥር ገደል የምንከተውና በቢድዐ የምንፈርጀው ቢሆን ኖሮ ከአኢማዎች ውስጥ የሚተርፍልን በቀለለ ነበር። አላህ ሁሉንም በችሮታውና በቸርነቱ ይዘንላቸው።” [አሲየር፡ 14/37-376]
ከዚህ የዘሀቢ ተግባር የምንረዳው ምንድነው? ኢብኑ ኹዘይማ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ማፅደቅ ግዴታ እንደሆነ መናገራቸውን አስረግጠዋል። ነገር ግን በዚህ ላይ የተሳሳቱ ሰዎችን በተመለከተ ኢብኑ ኹዘይማ በሄዱበት ርቀት (ማ^ክ^ፈ^ር) እንደማይገባ እየገለፁ ነው። የአላህን መገለጫዎች ተእዊል አድርጎ የተረዳ ሁሉ በዚህ መልኩ ቢያዝ ኖሮ እራሳቸው ኢብኑ ኹዘይማም አይተርፉም ነበር እያሉን ነው። ለዚህም ሐዲሠ ሱራን ተእዊል ማድረጋቸውን አነሱ።
3. አልባኒይ ረሒመሁላህ፦
ቢድዐ ላይ የወደቀ ሁሉ በሙብተዲዕነት ሊፈረጅ እንደማይገባ የተናገሩበት ብዙ ነው። ለሌላ ጊዜ በሰፊው መመለሴ ባይቀርም ለጊዜው አንድ ሁለት ንግግሮቻቸውን ልጥቀስ፡-
إذا كان هذا المخالف يخالف نصا أولا: لا يجوز اتباعه، وثانيا لا نبدع القائل بخلاف النص وإن كنا نقول إن قوله بدعة، وأنا أفرق بين أن تقول فلان وقع في الكف.ر وفلان كف.ر، وكذلك فلان وقع في البدعة وفلان مبت.دع، فأقول فلان مبت.دع مش معناه وقع في بدعة، وهو مَن شأنه أنه يبتدع، لأن مبت.دع اسم فاعل، هذا كما إذا قلنا فلان عادل ليس لأنه عدل مرة في حياته، فأخذ هذا اسم الفاعل، القصد أن المجتهد قد يقع في البدعة–ولا شك-لكن لا ألومه بها ولا أطلق عليه اسم مبت.دع، هذا فيما إذا خالف نصا
“ይሄ ተፃራሪ፡ በቅድሚያ መረጃን የሚፃረር ከሆነ ሊከተሉት አይፈቀድም። ሁለተኛ ከመረጃ ተቃርሮ የተናገረውን ንግግሩን ‘ቢድዐ ነው’ ብንልም ተናጋሪውን ሙብተዲዕ አናደርግም። እኔ ‘እከሌ ክህደት ላይ ወድቋል’ በማለትና ‘እከሌ ከ^ፍ^ሯ^ል’ በማለት መካከል እለያለሁ። ‘እከሌ ቢድዐ ላይ ወደቀ’ በማለትና ‘እከሌ ሙብ^ተዲዕ ነው’ በማለትም ላይ እንዲሁ። እናም እንዲህ እላለሁ፦ እከሌ ሙብ^ተዲዕ ነው ማለት ቢድዐ ላይ ወድቋል ማለት አይደልም ትርጉሙ። ይልቁንም ቢድዐ የሚያራምድ ማለት ነው። ምክንያቱም ሙብ^ተዲዕ የሚለው ቃል አድራጊ ነው። ይሄ ማለት ልክ ፍትሃዊው እከሌ እንደማለት ነው። ይሄ ግን በህይወቱ አንዴ በፍትህ ስለፈረደ ይህንን ስም ይዟል ማለት አይደለም። ዋናው ነገር ሙጅተሂድ የሆነ ሰው ያለ ጥርጥር ቢድዐ ላይ ሊወድቅ ይችላል። ነገር ግን በሷ አልወቅሰውም። ሙብ^ተዲዕ የሚል ስምም አልለጥፍበትም። ይሄ እንግዲህ ቀጥተኛ መረጃ ሲፃረር ነው።” [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር፡ 850]
ወንድሜ ሆይ! ንግግሮቻቸውን በደንብ አጢነህ እራስህን ገምግም። በተሳሳተ መልኩ ቀጥተኛ መረጃ በተፃረረ ላይ ይህንን ካሉ በኢጅቲሃድ ጉዳዮች የተሳሳተስ ላይ ምን የሚሉ ይመስልሃል?!
አሁንም ከአልባኒ ጋር እንቀጥል፦
“አንድ መሰረቱ የአህሉ ሱና መሰረት የሆነ፣ በዚያም ላይ የሚጓዝ የሆነ፣ ከሱና ሰዎች በመከላከልና መንገዳቸውን በማገልገልም የሚታወቅ የሆነ ሰው አልፎ አልፎ አንዳንድ የመንሃጅ ስህተቶች ቢንፀባረቁበት፡
* ከሱ ማስጠንቀቅ ነው የሚገባው? ወይስ
* ስህተቶቹን ግልፅ ማድረግ ነው የሚገባው?” ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ነበር የመለሱት፡-
“መልሱ ሁለተኛው ነው እንጂ የመጀመሪያው አይደለም።” (ስህተቶቹ ግልፅ ይደረጋሉ እንጂ ከሱ ማስጠንቀቅ አይገባም።) [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ካሴት ቁ. 751]
4. ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ፦
አንድ ሱናን መንገዱ ያደረገ ሰው የዐቂዳ ስህተት ብናገኝበት በቀጥታ በቢድዐ ፈርጀን ከሱና እናስወጣዋለን? ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን በንዲህ አይነት ጉዳይ ላይ ምን እንደሚሉ እንመልከት፡-
وأما الخطأ في العقيدة: فإن كان خطأ مخالفًا لطريق السلف، فهو ضلال بلا شك ولكن لا يحكم على صاحبه بالضلال حتى تقوم عليه الحجة، فإذا قامت عليه الحجة، وأصر على خطئه وضلاله، كان مبت.دعًا فيما خالف فيه الحق، وإن كان سلفيًّا فيما سواه
“የዐቂዳ ስህተትን በተመለከተ ለመልካም ቀደምቶች መንገድ ተፃራሪ የሆነ ስህተት ከሆነ እሱ ያለጥርጥር ጥመት ነው። ነገር ግን ባለዚህ ጥፋት መረጃ እስከሚቀርብበት ድረስ በጥመት አይፈረጅም። መረጃ ቀርቦበት በስህተቱና በጥመቱ ላይ የሚፀና ከሆነ ግን ሐቅን በጣሰበት ጉዳይ ሙብ^ተዲዕ ሆኗል። ከዚያ ውጭ ባለው ሰለፊ ቢሆንም።” [ኪታቡል ዒልም፡ 135]
ፅሁፌ ስለረዘመ የሌሎች ዓሊሞችን ንግግር አላካተትኩም። የምፅፈው በጉዳዩ ላይ የዑለማዎቹ አካሄድ ምን እንደሚመስል ማወቅ ለሚፈልጉ ጥቆማ ለመስጠት ያክል ነው። እርምት ያለው ካለ ከስር በአደብ ሃሳብ መለዋወጥ ይቻላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 24/2013)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor